አሜሪካ በኢትዮጵያ ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ለማጠናከር ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከግሉ ዘርፍ ጋር ውይይት አካሄደች

Date:

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ ጋር በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የጋራ ውይይት መርተዋል።

ውይይቱ የንግድ ዲፕሎማሲን ማጠናከር፣ የገበያ ተደራሽነትን ማስፋት እና በኢትዮጵያ ለሚሰሩ የአሜሪካ ኩባንያዎች ፍትሃዊ የንግድ ሁኔታ መፍጠር ላይ ያተኮረ ነበር።

አምባሳደር ማሲንጋ ግልጽ፣ ተጠያቂነት ያለውና ሊገመት የሚችል የንግድ አካባቢ መፍጠር የአሜሪካን ኢንቨስትመንት ለመሳብና በግሉ ዘርፍ የሚመራ የኢኮኖሚ እድገት ለማፋጠን ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ ላይ የአሜሪካ ንግድ ተቋማት ተወካዮች ያቀረቧቸው ችግሮችና መፍትሔ ሀሳቦች በመንግሥት ኃላፊዎች በቀጥታ ምላሽ ያገኙ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች ያሉባቸውን ማነቆዎች ለመፍታት የተግባር ዕቅድ እንዲያዘጋጁ ሐሳብ ቀርቧል።

አሜሪካ ይህ ትብብር የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማፋጠን፣ የንግድ እንቅስቃሴን ለማስፋትና ለሁለቱም አገራት ሕዝቦች የኢኮኖሚ ጥቅም ለማሳደግ እንደሚያግዝ ገልጻለች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኔታንያሁ እና ትራምፕ የፊታችን ማክሰኞ በዋይት ሀውስ እንደሚወያዩ ተገለጸ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፤ ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ...

የካፍ ፕሬዝዳንት የ2027 አፍሪካ ዋንጫ በ24 ተሳታፊ ሀገራት እንደሚካሄድ አስታወቁ

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሙትሰፔ የ2027...

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና መስጠት ጀመረ

ሆስፒታሉ በቀን ከ300 በላይ ታካሚዎችን ያስተናግዳል የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ...

የእነ ክርስቲያን ክስ ብይን ለሚቀጥለው ዓመት ተቀጠረ

በተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥበት የቆየው የእነ አቶ ክርስቲያን ታደለ...