ኢራን በኦማን ባሕረ ሰላጤ በመንቀሳቀስ ላይ የነበረን የአሜሪካ መርከብ መከልከሏ ተነገረ ። የኢራን ሃይሎች ረቡዕ እለት አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የባህር ኃይል ንብረት የሆነ የአሜሪካ አጥፊ መርከብ ቴህራን የዉሐ ክልል ዘልቆ ለመግባት ሲሞክር እንዳገኘች ገለፀች ።
የኢራን መንግስት ቲቪ እንዳስታወቀው ዩኤስኤስ ፌዝጀራልድ መርከቧ በኢራን ቁጥጥር ስር ወደ ሆነዉ ውሀ ክልል በመቅረብ ለመግባት ስትሞክር የኢራን ጦር ሄሊኮፕተር ማስጠንቀቂያ በመስጠት ማባረሩን ገልጿል ።
በተዘገበው የቪዲዮ ተገግፎ በወጣዉ መረጃ ምስል ላይ አንድ ሄሊኮፕተር ከመርከቡ ጋበቅርበት ሲበር ታይቷል ። እናም አንድ የኢራናዊ መርከበኞች በእንግሊዘኛ የሬዲዮ ማስጠንቀቂያ ለጦር መርከብ ሲሰጥ መንገዱን እንዲቀይር ትእዛዝ ሲሰጥ ይሰማል።
የአሜሪካ አጥፊ ‘Fitzgerald’ መርከብ በኢራን ቁጥጥር ስር ወደ ሆነዉ ውሃ ለመቅረብ መሞከሩ፣ ግጭት ቀስቃሽ እርምጃ ነው” ሲል የኢራን መንግስት ቴሌቪዥን ገልጿል።
የአሜሪካ መከላከያ ባለስልጣን የአሜሪካው መርከብ በአለም አቀፍ ውሃ ውስጥ በሚንቀሳቀስበት ወቅት ከኢራን SH-3 ‘Sea King’ ሄሊኮፕተር ጋር ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሙያዊ ግንኙነት ነበረው ብለዋል ።
የዩኤስ ጦር ባለፈው ወር የኢራንን የኒውክሌር ቦታዎችን ባደበደበ ጊዜ እስራኤል ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት ውስጥ እራሱን ማስገባቱ ተከትሎ የሁለቱ ሀገራት ግኑኝነት እየሻከረ ሲሄድ ኢራንም የኒኩሊየር መርሀ ግብሯን እንደማታቆም ደጋግማ እየገለፀች ይገኛል ።
የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ረቡዕ እለት በሰጡት ቃለ ምልልስ ቴህራን የኒውክሌር መርሃ ግብሯን ለሰላማዊ ዓላማ ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኗን እና ሀገራቸው ወደፊት እስራኤል ለምታደርገው ጦርነት ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል። ሲል ያስነበበው አልጀዚራ ነዉ ።
የኔቲ ቲዩብ
