ፈረንሳይ በመስከረም ወር ለፍልስጤም መንግስት በይፋ እውቅና እንደምትሰጥ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስታውቀዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ይህን የሚያደርጉ ከሆነም ፈረንሳይ ይህን በማድረግ የመጀመሪያዋ የG7 ሀገር ትሆናለች ።
ማክሮን በኤክስ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ በትክክለኛ መንገድ በኒውዮርክ በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል።
አሁን ላይ የሚያስፈልገው የጋዛ ጦርነት እንዲያበቃ ማድረግ እና ነዋሪዎችን መታደግ ነውም ብለዋል።
እንዲሁም አስቸኳይ የተኩስ አቁም፣ ሁሉንም ታጋቾች መልቀቅ እና ለጋዛ ህዝብ ትልቅ ሰብአዊ እርዳታ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ባሰፈሩት ፅሁፍ ጠቅሰዋል።
የፍልስጤም ባለስልጣናት የማክሮንን ውሳኔ የተቀበሉ ሲሆን የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ግን እርምጃው “ሽብርን ያበረታታል” ሲሉ መግለፃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም
