አራት ቤተሰቦቻቸውን በአደጋው አጥተው ለሌሎች መፅናኛ የሆኑት ሊቀመንበር

Date:

አቶ ዳመነ ደበበ የማዞ ዶይሳ ቀበሌ ሊቀመንበር ናቸው። ለበርካቶች መፅናኛ ሆነዋል፤ ምክንያቱም የህዝብ መሪ ናቸውና።

በማዞ ዶይሳ ቀበሌ በተከሰተው አሳዛኝ የመሬት ናዳ አደጋ አቶ ዳመና አራት ቤተሰቦቻቸው ቢያጡም ሕመማቸውን በሆዳቸው ችለው ሌሎችን በማጽናናት የብዙዎችን ትኩረትን ስበዋል።

እኚህ ተወዳጅ ሊቀመንበር መጋቢት 1/2018 ዓ.ም የመጀመሪያው ናዳ ተከስቶ በአካባቢው በብዙዎች ዘንድ ከበሬታ ያላቸውን አቶ “ኤራ የተባሉ አዛውንት ለማትረፍ ህዝቡ “ኤራ አላ ኤራ አላ” እያሉ ሲጮሁ ሰምተው ወደ ስፍራ ለነፍስ አድን ስራ ተገግኝቶ መገኘታቸውን ነግረውናል።

እንደ ህዝብ አገልጋይ አደጋ የደረሰባቸውን ዜጎችን ለማትረፍ ከስፍራዉ የደረሱው ሊቀመንበር ራሳቸው በናዳው ተውጠው በእግዚአብሔር ቸርነት እና በሰው እርብርብ ከተቀበሩበት በተዓምር ወጥተዋል።

በአደጋዉ ባለቤታቸውን፣ ወንድ ልጃቸው እና ልጅ አዝላ የነበረችውን ሴት ልጃቸውን በአጠቃላይ አራት ልጆችን ማጣታቸው የውስጥ ሕመም ሆኖባቸዋል።

በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ለራሳቸው ተጽናንተው ሌሎችን ማበርታት ኃላፊነታቸው ነውና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር የተጎዱ ዜጎችን ለማጽናናት ወደ ስፍራው ባቀኑበት ከአንደበታቸው የፈለቀው የመጽናናት መልዕክት ለብዙዎች ብርታት ሆኗል።

ታዲያ እኝህ ብርቱ የሕዝብ አገልጋይ የማዞ ዶይሳ ሕዝብን ለማበርታት ሃዘናቸውን በውስጣቸው ይዘው ሕዝብን በትጋት እያገለገሉ ይገኛሉ።

ዘጋቢ- ዱቡሻ ሚዲያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...