አቢሲንያ ባንክ ከ349 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር በላይ ብድር አቀረበ

Date:

አቢሲንያ ባንክ የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመፍታትና የገቢ ንግድን ለመደገፍ በበጀት  ዓመቱ 349 ሚሊየን 943 ሺህ 588 የአሜሪካ ዶላር ብድር ማቅረቡን አስታወቀ፡፡

ባንኩ ለደንበኞች ካቀረበው የምንዛሪ ድልድል ውስጥ በ3ኛው ሩብ ዓመት ከ1 ሺህ በላይ ደንበኞች ወደ ሀገር ውስጥ የገበያ ዕቃዎችን እንዲያስገቡ 189 ሚሊየን 82 ሺህ 861 ዶላር እንዲያገኙ ማድረጉንም ገልጿል፡፡

ይህም የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት እያደረገ ያለውን ከፍተኛ ጥረት እንደሚያሳይ ነው የገለጸው፡፡

በቀጣይም የውጭ ምንዛሪ ሀብትን በአግባቡ በማሥተዳደር እና ከሀገራዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጋር በማጣጣም የደንበኞቹን ፍላጎት ለሟሟላት እንደሚሠራ አረጋግጧል፡፡

በውጭ ምንዛሪ ድልድል ረገድ በኃላፊነት በመሥራት ለተረጋጋ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት እያበረከተ ያለውን አስተዋፅዖም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁሟል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...