የረጅም ርቀት አትሌቱ ጌታቸው ማስረሻ በተከለከለ አበረታች ቅመም (ዶፒንግ) ምክንያት የ4 ዓመት ከባድ እገዳ ተላለፈበት።አትሌቱ ሰኔ 7 ቀን 2026 በኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ በሰጠው ናሙና Phentermine/mephentermine የተሰኘ የተከለከለ ንጥረ-ነገር በሰውነቱ ውስጥ መገኘቱ በምርመራ ተረጋግጧል።
በዚህም መሰረት የመጀመሪያ ደረጃ ከሰኔ 10 ቀን 2026 እስከ ሰኔ 9 ቀን 2030 (ለአራት ዓመታት) ከማንኛውም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ታግዷል። ከሰኔ 7 ቀን 2026 ወዲህ ያስመዘገባቸው ውጤቶች፣ ሜዳሊያዎች፣ ነጥቦች እና የገንዘብ ሽልማቶች ሙሉ በሙሉ ተሰርዘዋል።
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ከስፖርት ሥነ-ምግባር ውጭ በሆኑ ድርጊቶች እና ከጀርባ በሚተባበሩ አካላት ላይ የሚወስደውን ጥብቅ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
