አቶ ጌታቸው ረዳ ትላንት በክልሉ ወቅታው ሁኔታ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ላይ ያነሷቸው አንኳር ነጥቦች፦

Date:

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ በክልሉ ወቅታው ሁ

👉 የፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል የሚያደርጋቸውን በጎ ስራዎች መጥቀስ በህወሓት ቡድን ዘንድ ተቀባይነት የሚያሳጣና በባንዳነት የሚያስፈርጅ ነው፣

👉 ይህ ኃይል የትግራይን ህዝብ የሰላምና የልማት አጀንዳ ነጥቆ የግርግርና የትርምስ አጀንዳ በመፍጠሩ ህዝቡ መስቀለኛ መንገድ ላይ እንዲቆም አድርጓል፣

👉 ሁሉም የትግራይ ህዝብ ህልውና የሚገደውና ለኢትዮጵያ ይጠቅማል ብሎ የሚያምን ህዝቡ ካጋጠመው ቀውስ እንዲወጣ የሚቻለውን ማድረግ አለበት፣

👉 የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዓላማዎች በክልሉ ሰላምና መረጋጋትን ማረጋገጥ፣ ለክልሉ የኢኮኖሚ መልሶ ግንባታ መሰረት መጣል፣ ቀጣይ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ የሪፎርም ስራዎችን ማከናወን ነው፣

👉 በክልሉ የተፈጠረው አለመረጋጋት የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋምና ወደ መደበኛ ህይወት የመመለስ ስራ ላይ እክል ፈጥሯል፣

👉 ከ75 ሺህ በላይ የቀድሞ ታጣቂዎች የተቋረጠው የመልሶ የማቋቋም ሂደት እንዲቀጥል እየጠየቁ ነው፣

👉 የፕሪቶሪያው ስምምነት ዓላማ ተኩስ ማቆም ነው፤ የፕሪቶሪያ ስምምነት በተሟላ ሁኔታ ከተተገበረ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሳይሆን በህዝብ የተመረተ መንግስት ነው ሊኖር የሚገባው፣

👉 የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋምና ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው፤ ለዚህ የፌደራል መንግስትም የበኩሉን ሚና መወጣት አለበት፣

👉 ትግራይ ውስጥ ያለው የጸጥታ ኃይል ስልጣንን ብቻ ማዕከል ያደረገው ትንሽ አባላት ያሉት ቡድን በሚፈጥረው ትርምስ ውስጥ መግባት አይፈልግም፣

👉 ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ያላቸው የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አካላት አሉ፤ ይህ ግንኙነት የትግራይን ህልውና እና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ አይጠቅምም፣

👉 በህወሓት ኃይሎች መካከል ለተፈጸመው ጥፋት የፌደራል መንግስትን ተጠያቂ ማድረግ አግባብ አይደለም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...