አዋሽ ባንክ እና አዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለኅብረተሰቡ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ የታገዙ ለማድረግ እና ወርሃዊ የውሃ ክፍያ ሥርዓትን ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ የውሃ ክፍያዎች በአዋሽ ባንክ የክፍያ አማራጮች እንዲሰጡ እና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ደንበኞችም ያለ ምንም ውጣ ውረድ ክፍያቸውን በሚፈልጉት የፋይናንስ ተቋም መክፈል እንዲችሉ ሁኔታዎችን የሚያመቻች መሆኑ ተገልጿል፡፡
ባንኩ የሚያቀርበው የቴክኖሎጂ መፍትሄ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ የሚያዘምን ፣ ብዙ የሰው ኃይል እና ከፍተኛ ወጪን የሚያስቀር መሆኑም ተጠቅሷል።
እንዲሁም ሌሎች ተቋማት በቀጥታ ከባንኩ ሲስተም ጋር ሲስተማቸውን በማገናኘት ደንበኞቻቸው የውሃ ክፍያ እንዲከፍሉ የሚያስችል የክፍያ መፈፀሚያ ቴክኖሎጂ ባንኩ በማቅረቡ ለባለሥልጣን መ/ቤቱ ሂሳብ የማስታረቅ ስራውን ከአዋሽ ባንክ ጋር ብቻ እንዲሰራ ያስችለዋል ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት የአዋሽ ባንክ ደንበኞች ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን በመላው ሀገሪቱ ባሉት ከ980 በላይ የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፎች መክፈል መቻላቸው ተጠቅሷል።
