በፓሲፊክ ውቂያኖስ አደንዛዥ ዕፅ እንደጫነ የተጠረጠረ መርከብ ላይ ጥቃት በመፈፀም ሁለት ሰዎችን መግደሉን ፔንታጎን አስታውቋል።
እንደ አሜሪካ የመከላከያ ዋና ፀሀፊ ፔት ሄግሰን ገለፃ መርከቧ በአሜሪካ የስለላ ድርጅት እንደ ተደረሰባትና አደንዛዥ ዕፅ ጭናለች ተብሎ በመታመኑ ጥቃት መፈፀማቸው አስታውቀዋል።
በጥቃቱ በመርከቡ የነበሩ ሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በአሜሪካ ወታደሮች ላይ የደረሰ ጉዳት ስላለመኖሩ አስታውቀዋል።
ከአውሮፓውያኑ መስከረም 2 ወዲህ አሜሪካ አደንዛዥ እፅ ጭነዋል ብላ ያመነችባቸውን ጀልባና መርከቦች ላይ ጥቃት ስትፈፅም የአሁኑን ጨምሮ ለስምንተኛ ጊዜ ሲሆን፤ በፓሲፊክ ውቂያኖስ ሲፈፀም ግን የመጀመሪያዋ ነው።
ዶናልድ ትራምፕ በአለምአቀፍ የውሀ መተላለፊያዎች የሚንቀሳቀሱ ህገወጥ መርከቦች ላይ እርምጃ የመውሰድ ህጋዊ መብት አለኝ ያሉ ሲሆን ይህንን ስልጣናቸውን ማስፉት ካሻቸው ወደ አሜሪካ ኮንግረስ እንደሚያቀኑ አስታውቀዋል።
አስተዳደራቸው ፀረ አደንዛዥ እፅ እንቅስቃሴዎችን በስፋት ለመጀመር መዘጋጀቱንም ገልፀዋል ትራምፕ።
ምክትላቸው ማርኮ ሩቢዮ በበኩላቸው በኦቫል ኦፊስ በነበራቸዎ መግለጫ መርከቦች ሲጋዩ ላለመመልከት የትኛውም ሀገር ወደ አሜሪካ አደንዛዥ እፅ መላኩን ማቆም ይገባዋል ብለዋል።
NBC Ethiopia
