አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ “በጥሩ ጤንነት ላይ” ይገኛሉ

Date:

አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ “በጥሩ ጤንነት ላይ” እንደሚገኙ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ተናገሩ።
የጠቅላይ መሪው ደኅንነት ጉዳይ ለቀናት መነጋሪያ ሆኖ ነበር።

ባለፈው ሳምንት ማገባደጃ ላይ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሞጅታባ ኻሜኒ “ጉዳት ቢደርስባቸውም” በሕይወት እንዳሉ ተናግረዋል።


የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በበኩላቸው ጠቅላይ መሪው በጥሩ ጤንነት ላይ እንዳሉ እና “ነገሮችን ሙሉ በሙሉ እየተቆጣጠሩ” እንደሚገኙ ገልጸዋል።


የኢራን ጠቅላይ መሪ ሆነው ከተመረጡ ወዲህ ላለፉት ሰባት ቀናት በአደባባይ አልታዩም። የመጀመሪያ ይፋዊ ንግግራቸው በቴሌቭዥን መሰናዶ አቅራቢ አማካኝነት የተነበበው ከሦስት ቀናት በፊት ነበር።


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ጦርነቱን የሚቋጭ ቀጣናዊ የድርድር ጥረትን” እንደሚደግፉ ተናግረዋል።
ሆኖም ግን ይሄንን ለማድረግ የሚያስችል ድርድር እየተካሄ አለመሆኑን ገልጸዋል።


ትራምፕ በበኩላቸው “ኢራን መደራደር ብትፈልግም አሜሪካ ዝግጁ አይደለችም” ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...