አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች የሚደረጉ ህዝባዊ ዝግጅቶች የፖለቲካ መድረኮች ሆነዋል

Date:

በሪፍት ቫሊ ኢንስቲትዩት “Urban contestation in Ethiopia” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው አውደ ጥናት ላይ በቀረበው ሪፖርት መሠረት፣ በአዲስ አበባን ጨምሮ በሀገሪቱ በሚገኙ ሌሎች ከተሞች የሚደረጉ እንደ አድዋ ድል በዓል፣ ኢሬቻ እና የታላቁ ሩጫ ያሉ ህዝባዊ ዝግጅቶች የፖለቲካ መድረኮች እየሆኑ መምጣታቸውን ተጠቁሟል።

በዚህ ሪፖርት ላይ እንደተገለጸው፣ እነዚህ ዝግጅቶች በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የፖለቲካ ትረካዎች የሚንጸባረቁባቸውና የታሪክ ትርጓሜዎች የሚፎካከሩባቸው መድረኮች ሆነዋል ይላል።

ጥናቱ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ሐዋሳ፣ ሆሳዕናን እንዲሁም ድሬደዋን ያካተተ ሲሆን በተለይም በአዲስ አበባ ላይ በተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በየጊዜው የሚደረጉ እነዚህ ዝግጅቶች የተለያዩ የፖለቲካ ትረካዎች የሚንጸባረቁባቸውና የታሪክ ትርጓሜዎች የሚፎካከሩባቸው መድረኮች ሆነዋል።

ከአድዋ ድል በዓል ጋር በተያያዘ የመንግስት ትረካ የንጉስ ምኒልክን አስተዋጽኦ ሲያጎላ፣ ተቃራኒ ትረካዎች ደግሞ ከታሪክ የተገለሉትን ሰዎች አስተዋጽኦ ያነሳሉ።

ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ እነዚህ ተፎካካሪ ትረካዎች አዎንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖዎች አሏቸው። በአንድ በኩል፣ ገንቢ ውይይትን ሊያበረታቱና ያለፈውን ጊዜ የተሻለ ግንዛቤ ላይ ሊያደርሱ ይችላሉ። በሌላ በኩል፣ ለፖለቲካ ጥቅም ሲውሉ ማህበራዊ ውጥረቶችን ሊያባብሱና እርቅን ሊያደናቅፉ ይችላሉ ሲሉ በጥናታቸው ላይ አስፍረዋል።

ጥናቱ ፖሊሲ አውጪዎች በሀገራዊ ውይይቶች ላይ የታሪካዊ የኃይል አለመመጣጠንን ከግምት ውስጥ እንዲያስገቡና ያለፉ በደሎችን ለመፍታት ጥረት እንዲያደርጉ ይመክራል።CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...