አጨቃጫቂው ውሳኔ አለፈ

Date:

የአሜሪካ ኮንግረስ ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትልቁ ድል  ነው የተባለውን አወዛጋቢ  ውሳኔ አሳለፈ።

ኮንግረሱ ያሳለፈው ውሳኔ አብዛኛውን ግብር ቅነሳ ቋሚ አድርጎ የሚያስቀጥል፣ለድንበር ደህንነት፣ለመከላከያ እና ሀይል ምርት ወጭ የሚጨምር አሊያም የሚያሳድግ ነው።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 218 ለ 214 በሆነ ድምጽ ያጸደቀ ሲሆን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገር ውስጥ አጀንዳ ትልቁ የፖሊሲ ድል ሆኖ ተመዝግቦላቸዋል።

ሁለት ሪፐብሊካኖች ብቻ ከዴሞክራቶቹ ጎን ቆመዋል፡፡

የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት(ሴኔት) ረቂቁን በጠባብ ውጤት 51 ለ 50 በሆነ ድምጽ ማሳለፉም ይታወሳል፡፡

ይህን ትንቅንቅ የሴኔት ውጤት ለማስመዝገብ የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት የጄዲ ቫንስ ገላጋይ ውሳኔን ይፈልግ ነበር፡፡

የአሜሪካ ሴኔት በምክትል ፕሬዚዳንቶች የሚመራ በመሆኑ የድምጽ ውጤቶች እኩል ሲሆኑ አሊያም ገላጋይ ሲፈልጉ ድምጻቸውን ለመስጠት ይገደዳሉ፡፡

ቫንስም ያደረጉት ይህኑ ነው፡፡

የትራምፕ ትልቁ ረቂቅ ህግ የ2017 ማለትም የቀደመ ፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው የተራዘመ የግብር ቅነሳ ሀሳብ ውጤት ነው፡፡

አከራካሪው እና ግዙፉ ረቂቅ ህግ(ቢግ ቢውቲፉል ቢል) በዴሞክራሮቹ የሚሊዮን አሜሪካውያን ህይወት ላይ የተላለፈ አደገኛ ውሳኔ ነው በሚል እየተብጠለጠለ ነው።

የኮንግረሱ የበጀት ቢሮ ረቂቁ 3.4 ትሪሊዮን ዶላር ለሚቀጥሉት አስርት ዓመታት በፌደራል ደረጃ ጉድለት ያመጣል ፤ሚሊዮኖችን ያለ ጤና መድህን ባዷቸውን ያስቀራቸዋል ብሏል፡፡

ዋይት ሀውስ እና ሪፐብሊካኖቹ ይህን መከራከሪያ ፈጽሞ አይቀበሉትም፡፡

ዴሞክራቷ ካማላ ሀሪስም ውሳኔውን
“ሪፐብሊካኖቹ በኮንግረሱ ውስጥ ሚሊዮኖችን  በመላ አገሪቱ ለማውደም ድምጽ ሰጡ ” በሚል አጣጥለውታል፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንም ውሳኔው ግድየለሽነት ብቻ ሳይሆን ጭካኔም ነው ብለውታል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን ዴሞክራቶቹ እኔንም ፤አሜሪካንም ይጠላሉ ግን ትልቁን ድል አሜሪካ አስመዝግባለች ሲሉ በኩራት ተናግረዋል፡፡

ትራምፕ በሚጓጉለት ረቂቅ ህግ ላይ ፊርማቸውን ያኖራሉ፤ፖሊሲያቸውን ለማስፈጸምም ዕድሉ እጃቸው ላይ ገብቷል፡፡

ዋሽንግተን ፖስት እና ሲ ኤን ኤን እንደዘገቡት።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...

በኢትዮጵያ በማሳደጊያ ተቋማት የሚገኙ ሕፃናት ቁጥር ወደ 12 ሺሕ ዝቅ አለ

በኢትዮጵያ በተለያዩ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት...