የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጠርቶት የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት ለ”ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።
ሰልፉን ኢሕአፓ አባል በሆነበት በትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ደረጃ ለማሳደግ መወሰኑን ፓርቲው የገለጸ ሲሆን፣ ሰላማዊ ሰልፉ መቼ እንደሚደረግ በቅርብ ቀን ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል።
“በኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ታስቦ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ከ[ትብብሩ] አባላት ጋር በመነጋገር ያደረገው ቢሆንም፣ አንድ አንድ አካላት ለመከፋፈያ ሲጠቀሙበት ነበር” ብለዋል።
“ትብብሩ በተናጥል እየሄደ ነው። ትብብሩ ፈርሷል፣ የፓርቲው ጤናማነት አደጋ ላይ ነው፣ በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እና የአባላት መከፋፈል ለመፍጠር ተሞክሯል” ያሉት መጋቢ ብሉይ አብርሃም “ልምድ ባላቸው ፖለቲከኞች መፍትሄ አግኝቷል” በማለት ገልጸዋል። አክለውም፣ “በመሆኑም አሁን ላይ የበለጠ እንዲጠናከር ስለፈለግን፣ የተጠናከረ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሰልፉን በቅንጅት ደረጃ ከፍ ለማድረግ ወስነናል” ብለዋል።
ቅንጅቱ ሰልፉን አንድ ጊዜ ብቻ የሚያደረግ ሳይሆን የቅስቅሳ ጊዜው እስከሚጠናቀቅበት ወቅት ድረስ በተደጋጋሚ በስታድየሞች እና በትልልቅ አደባባዮች ለማድረግ መወጠኑንም ጨምሮ ተናግሯል።
ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ
Date:
