ኢራን ከሞሳድ ጋር ግንኙነት ያላቸው ከ700 በላይ ዜጎች አሰረች

Date:

ኢራን ከእስራኤል የስለላ ድርጅት (ሞሳድ) ጋር ግንኙነት አላቸው ያለቻቸውን ከ700 በላይ ዜጎች በቁጥጥር ስር አውላለች፡፡

ባለፉት 12 ቀናት ብቻ ኢራን ከ700 በላይ ዜጎችን ከእስራኤል ጋር ግንኙነት በመፍጠር እያሴሩ ነው በሚል ጥርጣሬ ማሰሯን ፋርስ የዜና ወኪልን ዋቢ አድርጎ የዘገበው አርቲ ነው፡፡

በተጨማሪም ለእስራኤል ሲሰልሉ ተገኙ የተባሉ ሶስት ዜጎች በዛሬው ዕለት ርምጃ እንደተወሰደባቸው ተመላክቷል፡፡

በሌላ ዜና የኢራን የኒውክሌር ማመንጫ ጣቢያ ፎርዶው በአሜሪካ ቡንከር ቡስተር ቦምብ ሙሉ ለሙሉ ወድሟል ሲሉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትርምፕ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት ኢራን በኒውክሌር ጣቢያው ላይ ምንም አይነት የከፋ ጉዳት አለመድረሱን መግለጿን ተከትሎ ነው፡፡

እስራኤል በጉዳዩ ላይ መረጃ እንዳሰባሰበች የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ፥ በዚህም አሜሪካ ጥቃት የፈጸመችባቸው የኒውክሌር ጣቢያዎች ሙሉ ለሙሉ መውደማቸው ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራሟን ዳግም የምትጀምር ከሆነ አሜሪካ በድጋሚ ርምጃ ትወስዳለች ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...