የኤርትራው ፕሬዚዳንት በትናንትናው ዕለት ኤርትራ 34ኛ የነፃነት ቀኗን ስታከብር በአስመራ ስታዲየም ተገኝተው በትግርኛ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ኢትዮጵያን እና ምዕራባውያንን ወርፈዋል።
-“የውጭ ሀይሎች በብልፅግና ወኪላቸው አማካኝነት የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ላለፉት አምስት አመታት ያወጁት ጦርነት ምን ያህል ተስፋ እንደቆረጡ ያሳያል”
- “ሊያቀርቡ የሚፈልጓቸው ምክንያቶች; ናይል እና ቀይ ባህር፣ የባህር በር ማግኘት፣ የኦሮሞ ህዝብን የማይወክል የኦሮሙማ አስተሳሰብ፣ የኩሽ እና የሴም ግጭት… ናቸው”
- “የኢትዮጵያ ህዝብ የራሱን ምርጫ መርጧል፣ ተቃውሞውን ለማጠንከር እየተዘጋጀ ነው”
-“የኦሮሞን ህዝብ በትክክል መወከል የተሳነው የ”ኦሮሙማ” አስተሳሰብ በመላ ሀገሪቱ የብሄር ግጭቶችን እያቀጣጠለ ነው”።
-“በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል የነበረው ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ፈርሷል፣በወቅቱ ለብልፅግና መንግሥት ያደረግነው ድጋፍ ግን አይፀጥተንም”
-“የኢትዮጵያ ህዝብ ሌላ አገዛዝ የሚታገስበት ሁኔታ እስኪፈጠር ድረስ በተለያዩ መንገዶች ተቃውሞውን እያሰማ ነው”።
-“አሁን ላይ ትኩረታችን ልማትና እድገት ነው፣ ሀገር ከመመስረት የሚያግደን ምንም ነገር የለም”ሲሉ ነው የተደመጡት።
