ኢባትሎ በ 2017 በጀት ዓመት ከ108 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

Date:

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት (ኢባትሎ) በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት 108.78 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር በሪሶ አመሎ አስታወቁ። ይህ ገቢ ድርጅቱ ካቀደው 101.86 ቢሊዮን ብር በ107 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑ ተገልጿል።

ዶ/ር በሪሶ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ኢባትሎ በበጀት ዓመቱ 3.7 ሚሊዮን ቶን ገቢ ጭነት እና 40 ሺህ ቶን ወጪ ጭነት በራሱና በኪራይ መርከቦች አጓጉዟል። በተጨማሪም 108 ሺህ TEU ኮንቴይነሮችን በመልቲሞዳል ሲስተም እንዲሁም 2.2 ሚሊዮን ቶን ገቢ ጭነት እና 356 ሺህ ቶን ወጪ ጭነት በዩኒሞዳል ሲስተም ማጓጓዙን ገልጸዋል።

በአጠቃላይ 437 ሺህ TEU ኮንቴይነሮች በደረቅ ወደቦችና ተርሚናሎች መስተናገዳቸውን አስታውቀዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው በቀይ ባህር አካባቢ የነበረው የጸጥታ ችግር ፈተና እንደነበር የገለጹ ሲሆን፣ ድርጅቱ የራሱን መርከቦች የጉዞ መስመር በማጠፍ እና ሌሎች ስትራቴጂዎችን በመተግበር ጭነቶችን በተፈለገው ፍጥነት ማጓጓዝ እንደቻለ አብራርተዋል።

ለተገኘው ከፍተኛ ገቢ የሀገር በቀል ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሚና እንደነበረው የገለጹት ዶ/ር በሪሶ፣ ድርጅቱ የውጭ ምንዛሪ ገቢን ለማሳደግ በሌሎች አገራት ወደቦች መካከል የሚሰጠው የጭነት ማጓጓዣ አገልግሎት፣ የዲጂታላይዜሽን ስራዎች፣ የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክስ ስልጠና አገልግሎት እድገት አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ጠቅሰዋል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...