ኢትዮጵያ በፕሬስ ነጻነት 145ኛ ላይ ተቀመጠች

Date:

በፕሬስ ነጻነት ከኢትዮጵያ በታች ያሉ የ

ምስላዊ መረጃ:- ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (RSF) በየዓመቱ የ180 ሀገራትን የፕሬስ ነጻነት በመመዘን ያስመዘገቡትን ደረጃ ይፋ ያደርጋል። ድርጅቱ በትላንትናው ዕለት ባወጣው የዘንድሮው ዝርዝር ኢትዮጵያ 145ኛ ደረጃ አግኝታለች። ይህ ውጤት ሀገሪቱ አምና ከነበረችበት በአራት ደረጃዎች መውረዷን ያመለከተ ሆኗል።

በድርጅቱ ዝርዝር መሰረት የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ዘንድሮም “በጣም አሳሳቢ” በሚባለው ውስጥ ምድብ ውስጥ የሚገኝ ነው። ከዓለም ህዝብ ከግማሽ በላይ የያዙ 42 ሀገራት በዚሁ ምድብ ውስጥ የሚገኙ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል። እነዚህ ሀገራት የጋዜጠኝነት ሙያን መተግበር “አደገኛ የሆነባቸው” አሊያም ደግሞ የፕሬስ ነጻነት “ከእነአካቴው የሌለባቸው” እንደሆኑ ድርጅቱ ገልጿል።

ኢትዮጵያ በRSF ዝርዝር የመጨረሻዎቹን ደረጃ ከያዙ ሰባት የአፍሪካ ሀገራት ውስጥም ተካትታለች። ኢትዮጵያን ተከትላ በ146ኛ ደረጃ የተቀመጠችው ሩዋንዳ ናት። ሁለቱ የኢትዮጵያ ጎረቤቶች ሱዳን እና ጅቡቲ እንደ ቅደም ተከተላቸው 156ኛ እና 168ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ግብጽ 170ኛ ደረጃን አግኝታለች። ሌላኛዋ የኢትዮጵያ ጎረቤት ኤርትራ እንደ አምናው ሁሉ በድርጅቱ ዝርዝር የመጨረሻውን 180ኛ ደረጃ ይዛለች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...