በቻይና ናንጂንግ ከተማ ሲካሄድ በቆየው 20ኛው የዓለምየቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም ደግሞ 3ኛ ሆና ውድድሩን አጠናቃለች።
ኢትዮጵያ በውድድሩ ሁለት የወርቅ እና ሶስት የብር ሜዳልያዎችን ማግኘት ችላለች።
በሴቶች 3000 ሜትር አትሌት ፍረወይኒ ኃይሉ እንዲሁም በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝተዋል።
አትሌት በሪሁ አረጋዊ በወንዶች 3000 ሜትር፣ አትሌት ድርቤ ወልተጂ በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር እንዲሁም አትሌት ንግስት ጌታቸው በሴቶች 800 ሜትር ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶች ናቸው፡፡
