ኦፕን ኤ.አይ ዓመታዊ ገቢውን  ወደ 1 ትሪሊዮን ዶላር ለማሳደግ አቅዷል

Date:

ኩባንያው በዓመት 13 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ እየሰበሰበ ሲሆን፤ በቀጣይ አምስት አመታት ይህንን ገቢ ወደ 1 ትሪሊዮን ዶላር ለማድረስ ማቀዱን አስታውቋል፡፡

 70 በመቶ የሚሆነውን ገቢውን የሚሰበስበው ሰዎች ከኤ.አይ ጋር ለሚያደርጉት የሃሳብ ልውውጥ ከሚከፍሉት ወርሃዊ ክፍያ ነው፡፡

800 ሚሊዮን መደበኛ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ከሚገመተዉ ቻት ጂፒቲ፤ አምስት በመቶ የሚሆኑት ቋሚ ተመዝጋቢዎች ብቻ ናቸዉ ክፍያ የሚፈጽሙት፡፡ ይህም ገቢው ዝቅ እንዲል አድርጎታል ይላል ኩባንያዉ – ይህንን ማሳደግ አንዱ ስራ መሆኑን በመጠቆም፡፡ 

ቴክ ክረንች እንደዘገበዉ፤ ኩባንያው በቀጣዩ የአምስት ዓመት ዕቅዱ፣ አዳዲስ የኤ.አይ አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች በማቅረብ 1 ትሪሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዷል።

ኦፕን ኤ.አይ ያለመዉን ገቢ ለማግኘትና ተደራሽነቱን ለመጨመር በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ውስጥ ከ1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ለማድረግም ማቀዱን የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት አስነብቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...