ኧረ ፋታ ስጡን?!

Date:

መንግስት ግን” ምን ሁኑ ?” ሊለን ነው :: አጀንዳ እየደራረበና እያፋጠነ በመስጠት የሚያወዛግበን !?

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው ወር አላስቆጠረም :: በዚህ ምክንያት ጣሪያ የነካው የኑሮ ውድነት ናላውን ያዞረው ዜጋ ግራ በተጋባበት ስዐት መንጃ ፍቃድ እንደ አዲስ ትፈተናላችሁ አለና ክፍያ ያሳሰበውን ምድረ አሽከርካሪ አንጫጫው ::

ከኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ በጭንቀት የተሞላው ውክቢያ ሳይረግብ አስደንጋጭ የአዲስ ታርጋ ዋጋ ክፍያ አጀንዳ ተከተለ :: ምን ጉድ ነው !?

ዜጋው በእንዲህ ያለ ውክቢያ ግራ ሲጋባ : መንግስት ለዜጎች አሳቢ መስሎ ” የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋን እኔ ነኝ የምወስነው” እያለን ነው ::

ሀሳቡ ባልከፋ :: ግን እሱ በየጊዜው የሚጨምረው የነዳጅ ዋጋና እሱን ተከትሎ የሚግተለተለው የኑሮ ውድነት ቤት እያከራየ የሚተዳደረውን ዜጋ እይመለከተውም ይሆን ?!

እንዲህ ማሰቡ ካልቀር ህዝቡም እንዲተሳሰብ እሱ የሚዘውረውን የጭማሪ ማርሽ ለምሳሌ በቤትና በይዞታ ላይ የሚጨመረውን የግብር ልክና መልክ ለምን አያየውም !? ( ልብ አድርጉ ገና የፕሮፐርቲ ታክስ ሊመጣ መሆኑም አይዘነጋም )::

ሌላው ቀርቶ እስከ ቅርብ ጊዜ የፈለከውን ይህል ጊዜ ቆመህ ለሰፈር ወጣቶች አስር በር ብቻ የምትከፍልበት ፓርኪንግ መንግስት ጣልቃ ሲገባበት በትንሹ 40 ብር ደርሷል :: አንድ ደቂቃ እንኳ ብታሳልፍ ደግሞ ተጨማሪ የምትከፍለው በመነሻው ዋጋ ልክ ነው :: መኪና መጠቀም የማይቻል በት ደረጃ እየተደረሰ መስሏል::

እንዲህ እንዲህ እያልን መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ያለው ዜጋ የሚብከነከንበትን ብዙ ጉዳይ ማንሳት ይቻላል :: ግራ ገባን እኮ ጎበዝ !? እባካችሁ ፉታ ስጡን?!

( ጋዜጠኛና የህግ ባለሙያ ሳሙኤል ፍቅሬ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...

“ንባብ ለህይወት!” ታላቅ የንባብ ሳምንት እና የመጻሕፍት አውደ ርዕይ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት እና የንባብ ለህይወት...

በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ጋር ይኖራሉ

በኢትዮጵያ ከ10 ሚልዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ እና ከ2...