ከ1 ሺሕ በላይ ተቋማት እና ግለሰቦች የወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

Date:

የምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 ድንጋጌዎች ጥሰው የተገኙ ከ1 ሺሕ በላይ ተቋማት እና ግለሰቦች የወንጀል ክስ እንደተመሰረተባቸው የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አስታወቀ።

በዚህም የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ከባለስልጣኑ ሳይስጣቸው ወይም በሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ምርት ያመረቱ፣ ወደ ሀገር ያስገቡ እና ያከፋፈሉ፣ የተበላሸ ቆርቆሮ ወተት ለገበያ ያቀረቡ፣ ምግብን ከባዕድ ነገር ጋር የቀላቀሉ፣ የአልኮል ምርት ያስተዋወቁ፣ የሺሻን ምርት መጠቀም እና የሸጡ እንዲሁም ያልተመዘገበ መድኃኒት ያስገቡና በሸጡ ከአንድ ሺሕ 11  ተቋማት እና ግለሰቦች ላይ ወንጀል ክስ መመሥረቱን ባለሥልጣኑ አስታውቋል።

የክስ መዝገቡም በአዲስ አበባ በሚገኙ ሁሉም ክፍለ ከተማ ፍትሕ ጽ/ቤት 813 የወንጀል መዝገቦች፤ በባለሥልጣኑ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በሚገኙባቸው ክልሎች 122 እና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ 59 እና በተጨማሪም በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተማ በምርመራ ላይ የሚገኙ 17 መዝገቦች መሆናቸው በባለሥልጣኑ የሕግ ክፍል ባለሙያ የሆኑት ፍሬሰላም ዮሴፍ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ሕግ ባለሙያ የክስ መዝገቦች ያሉበት ሁኔታ ሲያስረዱ፤ ውሳኔ የተሰጣቸው 650 ሲሆኑ፣ ምርመራ ላይ የሚገኙ ደግሞ 56 እንዲሁም በተጨማሪም ምስክር እና ተከሳሽ ባለመቅረቡ ወይም ማስረጃ ባለመኖሩ የተዘጉ ወይንም የተቋረጡ ደግሞ 305 መሆናቸው ጠቁመዋል።

የክስ መዝገቦች አሃዛዊ መረጃ በባለሥልጣኑ በአዋጅ 1112/2011 መሠረት ባለስልጣኑ በመደበኛ የቁጥጥር ሥራዎች፣ ባለስልጣኑ ከክልል የጤና ተቆጣጣሪ ዎች ጋር በጋራ በተሰሩ የቁጥጥር ሥራዎች ፣ ከህብረተሰቡ ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ፣ እና በፖሊስ ድንገተኛ ፍተሸዎች ክስ የተመሰረቱ መሆናቸውን አብራርተዋል።

የወንጀሎቹም አዋጅ ተድቆ ወደ ሥራ ከተገባበት ከ2012 ጀምሮ፤ ባለፉት 5 ዓመታት ቁጥጥር ከሚደረግባቸው ምርቶች ጋር በተያያዘ የተመሰረቱ እንደሆነም አስታውሰዋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሕብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ እየሰጣቸው ከሚገኙ አገልግሎቶች በተጨማሪ፤ ሕገ-ወጥ የጤና ግብዓቶችና የምግብ ምርቶች ዝውውርን ለመግታት የኢንተለጀንስና ሕገ-ወጥ ንግድ መከላከል መሪ ሥራ አስፈፃሚ በማቋቋም ከብሔራዊ ደህንነት፣ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከኢንተርፖል፣ ከጉምሩክ ኮሚሽን፣ ከክልል የጤና ተቆጣጣሪ አካላትና ከየክልሉ ፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር በመሆን የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በዚህም በርካታ ሕገ-ወጥ ምርቶችን በመያዝ ማስወገድ ተችሏል ብለዋል፡፡

በተለይ ሕገ-ወጥ መድኃኒቶች ወደ ገበያ ሲገቡ ጥራታቸው፣ ደህንነታቸውና ፈዋሽነታቸው ባለመረጋገጡ በሕብረተሰብ ላይ ሁለተናዊ ሊባል የሚችል የጤና፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳትን እንደሚያስከትሉ ተመላክቷል።

“ይህንን ታሳቢ በማድረግ የቁጥጥር ሥራዎች በአጽንኦት እየተሰሩ ነው” ሲሉ የሕግ ክፍል ባለሙያው አሳስበዋል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...