የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት በሚመራው ተቋም ውስጥ ብቻ ከ1000 በላይ ኢትዮጵያዊያን የቻይንኛ ( መንዳሪ ) ቋንቋ እየተማሩ መሆኑን ተቋሙ ለቲክቫህ ገልጿል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ብሩክ ከድር በአሁኑ ጊዜ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በሌሎች ዘርፎች ካለው ጠቀሜታ የተነሳ የቻይና ቋንቋን የመማር ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ” ከ1 ሺህ በላይ በፌደራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዮት ስር የሚማሩ ይኑሩ እንጂ በሌሎቹም ተቋማት ቋንቋውን የሚማሩ በርካቶች ስለመኖራቸው አመላክተዋል።
ዳይሬክተሩ ምን አሉ?
የቻይና ቋንቋ የሚሰጠው በብዙ ቦታዎች ነው፣ ለአብነት ያክል በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ በፌደራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት እና በአጫጭር የስልጠና ማዕከላት ጭምር እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል ዶክተር ብሩክ።
አክለውም ” ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት የቻይና ቋንቋ በሰፋት እየተሰጠ ነው፣ በተለይም አሁን ላይ በበለጠ ጥልቀት እና ስፋት እያገኘ ስለመሆኑ አንስተዋል።
የቻይናን ቋንቋበሀገራችን መሰጠቱ ምን ፋይዳ አለው?
የቻይና ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ነው፣ ለዚህ ደግሞ ቋንቋውን መስጠታችን በተለያዩ ኢንዳስትሪ ውስጥ የስራ እድሉን በስፋት እንዲያገኙ አድርጓል፣ በተጨማሪም ኢንቨስትመንት እንዲስቡ፣ እንዲግባቡ እና የተግባቦት መጠን አንዲጨምር አድርጎታል ሲሉ አስረድተዋል።
የቻይና ቋንቋ ( መንዳሪ )የተባበሩት መንግስታት የስራ ቋንቋ ሆኗል፣ በአለም ላይ ደግሞ ከፍተኛ የተናጋሪ ቁጥር አለው፣ ኢትዮጵያ ውስጥም የተናጋሪው ቁጥር እየጨመረ ነው፣ ይህንንም የበለጠ ለማሳደግ እና አለም አቀፋዊነት እንዲያብብ ቢሮው እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
አለም አቀፍ የቻይንኛ ቋንቋ ቀን በትናንትናው እለት በፌደራል ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
@Tikvahethmagazine
