በአዳማ ከተማ አስተዳደር በመንግስት፣በዜግነት አገልግሎት በተጨማሪም በህዝብ ተሳትፎ የተገነቡ በአጠቃላይ 4ሺህ 2 መቶ 63 ፕሮጀክቶች የምረቃ ስነ ስርዓት እየተከናወነ ይገኛል።
በአጠቃላይ ከ17 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የህክምና ተቋማት፣የአስተዳደር ፅ/ቤቶች በተጨማሪም ት/ቤቶችን ጨምሮ ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ናቸው የተመረቁት።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ በኦሮሚያ ክልል በም/ፕሬዝዳንት ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ አዲሱ አረጋ፣ የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሀይሉ ጀልዴ እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
