የኳታሩ ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ እስራኤል በሶሪያ ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ኮንነዋል፡፡
ከሶሪያው ፕሬዚዳንት አህመድ አል ሻርዓ ጋር በስልክ ሲወያዩ ነው አል ታኒ እስራኤልን ያወገዙት፡፡
የእስራኤል ጥቃት የሶሪያን ሉዓላዊነት የጣሰ እና
የዓለም አቀፉን ህግ እንዲሁም የመንግስታቱ ድርጅትን ቻርተር ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው ብለዋል ኢሚሩ፡፡
የአል ጁላኒ መንግስት የውስጥ አንድነቱ የተጠበቀ እንዲሆን እና የአገሪቱን ዳር ድንበር በማስከበሩ ረገድ አቅም ከመፍጠር አንጻር ዶሃ ከጎኑ እንደምትቆምም አረጋግጠዋል።
ኳታር እስራኤልን እና ሃማስን በማደራደር ከፍተኛ ሚና ያላት አገር በመሆኗ በመካከለኛው ምስራቅ ያላት ተጽዕኖ በቀላሉ የሚታይ እንዳልሆነም ተዘግቧል።
ቀጠናዊ መረጋጋት መፍጠር ኳታር ቅድሚያ የምትሰጠው ጉዳይ ስለመሆኑም በሁለቱ መሪዎች የስልክ ውይይት ወቅት ተወስቷል፡፡
እስራኤል በመሀል ደማስቆ የሶሪያ መንግስት መከላከያ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤትን ቤተ መንግስቱ አቅራቢያ መደብደቧ አይዘነጋም ሲል የዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡
