ዘመን ገበያ አዲስ አመት ኤግዚቢሽን እና ባዛር በታሜሶል ኮሚዩኒኬሽን አዘጋጅነት ሊካሄድ ነው

Date:

የ2017 ዓ.ም የዘመን ገበያ አዲስ አመት ኤግዚቢሽንና ባዛርን ለማዘጋጀት ታሜሶል ኮሚዩኒኬሽን በ92.8 ሚሊዮን ብር ጨረታ ማሸነፉ ተገልጿል ።

ይህ ትልቅ ዝግጅት “ዘመን ገበያ አዲስ ነገር በአዲስ ዓመት ኤክስፖ 2018” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከነሐሴ 17 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል።

ዝግጅቱ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በሽርክና የሚዘጋጅ ሲሆን፣ የቴሌብር ሱፐርአፕን ለህብረተሰቡ በስፋት ለማስተዋወቅ ታስቦበት እንደሆነም ታውቋል።

በኤግዚቢሽኑ ላይ ከ300 በላይ የአገር ውስጥ ነጋዴዎችና አገልግሎት ሰጪዎች የሚሳተፉ ሲሆን፣ ከህንድ፣ ከቱርክ፣ ከቻይና፣ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ከሌሎች ሀገራት የመጡ ኤግዚቢተሮችም እንደሚገኙበት ተገልጿል።

የኤግዚቢሽኑ ተሳታፊዎች ለህብረተሰቡ ሰፊ ምርጫ የሚያቀርቡ ሲሆን፣ ከትምህርት ቁሳቁስ፣ የቤት እቃዎች እና ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የፍጆታ ዕቃዎች ይቀርባሉ ተብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ፣ ዋና ዋና ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት የሚገኙበት ልዩ “ፋይናንስ መንደር” የሚል ቦታ መዘጋጀቱ በዝግጅቱ ላይ ተጨማሪ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጃ ነጻነት አዋጅን በሙሉ ድምፅ አጸደቀ

በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ...

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...