እሁድ ግንቦት 24 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ለመጀመሪያ ጊዜ በተከናወነው እልል ያለ ሽልማት ፕሮግራም ዘኩራ የማስታወቂያ ድርጅት ምርጥ ማስታወቂያ ድርጅት የሚል ሽልማት ተቀብሏል፡፡
በታዋቂው የማስታወቂያ ባለሙያ ዘላለም ኩራባቸው የሚመራው ዘኩራ ማስታወቂያ ለዚህ ሽልማት የበቃው እያቀረባቸው ባሉት የኢትዮ ቴሌኮም ማስታወቂያዎች ነው፡፡
ሽልማቱን የዘኩራ ሚዲያና ማስታወቂያ ዳይሬክተር የሆነው ምሳሌ ሰለሞን መቀበሉን ለመረዳት ችለናል፡፡
ዘላለም ኩራባቸው በማስታወቂያ ዘርፍ ለአመታት የሰራና አሁን ዘርፉን በቀዳሚነት እየመራ ያለ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የፊልምና ማስታወቂያ ዳይሬክተር #ምሳሌ ሰለሞን በማስታወቂያ ዘርፍ የኢትዮ ቴሌኮምን የ130 ዓመታት ታሪካዊ ጉዞ በሚያስቃኘው የቲቪ ማስታወቂያ ስራ የአሸናፊነት ክብC እንዳቀዳጃቸው ተናግሯል ።
የዘኩራ ሚዲያና ማስታወቂያ መሥራች እና CEO
ዘላለም ኩራባቸው ለዳይሬክተር ምሳሌ ሰለሞን “ዳጎሰ ” ያለ ሽልማት መቀበሉ ተሰምቷል ።
