የ2018 የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና  ምዝገባ ይካሄዳል

Date:

በ2018 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ከመስከረም 20 እስከ 25 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት አመልካቾች የመመዝገቢያ ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት በ https://ngat.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ እንደሚችሉ የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ ገልጿል።

አመልካቾች ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ለሚኖራቸው ጥያቄ ዘወትር በሥራ ሰዓት በ0920157474 ወይም 0911335683 እንዲሁም በኢሜይል አድራሻ ngat@ethernet.edu.et በኩል ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ሁሉም አመልካቾች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሊኖራቸው እንደሚገባም ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በተጨማሪም አመልካቾች የምዝገባ እና የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር በቴሌብር (TeleBirr) በኩል ብቻ መከፈል እንደሚኖርባቸው ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...