በአዲሱ የትምህርት ዘመን ትምህርት ሚኒስቴር እያስገነባቸው ካሉ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የተወሰኑት በመጪው የትምህርት ዘመን ስራ እንደሚጀምሩ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታውቀዋል ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞ በሰጡት ማብራሪያ እንዳስታወቁት፤ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የበቁ የነገ የዚች ሀገር መሪ መሆን የሚችሉ ዜጎችን ለማፍራት የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቹ ከሁሉም አካባበዎች የሚመጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው፣ አብሮ መኖርና ማደግን የሚለምዱባቸውና የአገሪቱ የወደፊት መሪዎችን የምናፈራባቸው ቦታዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡
በዚህም መነሻ የትምህርት ሚኒስቴር በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች እያስገነባቸው ካሉ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ድረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የተወሰኑትን በመጪው የትምህርት ዘመን ስራ ለማስጀመር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ በተገነቡት የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2017 የትምህርት ዘመን 8ኛ ክፍል ካጠናቀቁ ተማሪዎች መካከል መልምሎ ለማስገባት ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ሲሆን፤ ለዚህም ተማሪዎች ተገቢውን መስፈርት አሟልተው እንዲጠባበቁ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል።
