ህወሃት ምርጫ ቦርድ ህወሃትን ከፓርቲነት የሰረዘበት መንገድ ተቀባይነት የለውም ያለ ሲሆን ምርጫ ቦርድ ለአንድ ወገን ያደላ ውሳኔ አሳልፏል ብሏል።
ህወሃት ችግሮችን ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በድርድር እና በንግግር ለመፍታት ተደጋጋሚ ጥያቄ ብናቀርብም ፍቃደኛ የፌደራል መንግስቱ ዳተኝነት አሳይቷል ብሏል።
በዚህም የምርጫ ቦርድ ለአንድ ወገን ያደላ ውሳኔ የፕርቶሪያውን ስምምነት አደጋ ውስጥ ጥሎታል ያለ ሲሆን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ለፌደራል መንግሥቱ እንዲሁም ለአደራዳሪዎቹ የሚከተለውን ጥሪ አቅርቧል።
1ኛ:- በፌደራል መንግሥቱ እና በህወሓት መካከል አስቸኳይ የፓናል ውውይት እንዲካሄድ ጫና እንዲደረግ
2,የአፍሪካ ህብረት የፀጥታው ምክር ቤት ይሄን ጉዳይ አጀንዳ እንዲያደርገው እና በቀጣይ ስብሰባ ሲቀመጥ እንዲወያይበትና የምርጫ ቦርድን ውሳኔ እንዲመረምር፣
3, ውይይት እስከሚደረግ የፌደራል መንግሥቱ የምርጫ ቦርድን ውሳኔ እንዲሰርዝ ጫና እንዲያሳድር እና ግፊት እንዲያደርግ “ጠይቋል።
