የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ በአዲስ አርማ (ሎጎ) ወደ ሥራ መግባቱን አስታወቀ

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ቀደም ሲል ይጠቀምበት የነበረውን ሎጎ (አርማ) በአዲስ መቀየሩን ይፋ አድርጓል።

ኤጀንሲው ይህንኑ አዲስ ሎጎ በማስተዋወቅ አጠቃላይ ተገልጋዮች፣ የሴክተር መሥሪያ ቤቶችና ባለድርሻ አካላት ተቋሙ በታደሰ መንፈስ ለላቀ አገልግሎት መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

ይህ የተቋሙ የሎጎ እና የብራንዲንግ (Branding) ለውጥ የውጫዊ ገጽታ መቀየር ብቻ ሳይሆን፣ ኤጀንሲው እያካሄደው ያለው ሰፊ የተቋማዊ ሪፎርም (የለውጥ እንቅስቃሴ) ዋነኛ አካልና ማሳያ መሆኑም አስታውቋል።

ኤጀንሲው ተገልጋዮቹን በታላቅ ትሕትና ለማገልገል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

ኅብረተሰቡ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኤጀንሲው ሲመጣ ማንኛውም ዓይነት መጉላላት ቢገጥመው፣ አልያም ሕገ-ወጥ አሠራር ቢመለከት ወይም አስተያየትና ጥቆማ መስጠት ቢፈልግ 6577 የተቋሙ የነጻ የስልክ መስመር በመደወል መረጃ መስጠት እንደሚችል ኤጀንሲው አሳስቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዜጋዬ ተገድሏል ያለችው ጋና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ ገባች

አንድ ጋናዊ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ካለው ፀረ ስደተኞች ተቃውሞ...

«የማይናገረው ልዑል» መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ሊመረቅ ነው

ደራሲ መሠረት ክንፈ ኃይሌ ከኦቲዝም ጋር ከሚኖረው ልጇ ልዑል...

በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚደረግ ንግድ በገንዘብ መጠን ተገደበ

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚከናወነውን...

(IMF) ከ460 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር አፀደቀ

አዳዲስ ብድር በመውሰድ ረገድ ጥንቃቄ እንድታደርግ ኢትዮጵያን ያስጠነቀቀው IMF...