የመከላከያ ሠራዊት አባላት በእሥራት ተቀጡ

Date:


በህገ ወጥ የሠዎች ዝውውር ተሠማርተዋል የተባሉ አንድ ከፍተኛ የአገር መከላከያ ሠራዊት አዛዥን ጨምሮ ሁለት የሠራዊቱ አባላት በ8 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት ተቀጡ፡፡


አባላቱ ቅጣቱ የተላለፈባቸው ትናንት በአርባምንጭ ከተማ በተሰየመው የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባሳለፈው የፍርድ ውሳኔ ነው ፡፡
ቅጣቱ የተወሰነው በሠራዊቱ የደቡብ ዕዝ 202ኛ ኮር 1ኛ ሬጅመንት አዛዥ ሻምበል መብራቱ ታዴ እና በሬጅመንቱ የኦራል አሽከርካሪ በሆነው ወታደር ጌታቸው ክብረት በተባሉት ላይ ነው ፡፡


አዛዡ እና የሰራዊቱ አባል ቅጣቱ የተወሰነባቸው ህዳር 16 2016 ዓ.ም 52 ኤርትራዊያንን በሠራዊቱ የኦራል ተሽከርካሪ በመጫን ወደ ኬኒያ በማሻገር ላይ እንዳሉ በመያዛቸው መሆኑን የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ ጮራ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል ፡፡


የፌደራል ፍትህ ሚኒስቴር ዐቃቤ ህግ ክሱ በውክልና በጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲታይለት ባቀረበው የክስ መዝገብ መሰረት የተከሳሾቹን ጉዳይ ሲመለከት መቆየቱን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ “ ተከሳሾቹ የሰዎች ዝውውር ወንጀሉን የፈጸሙት ለግዳጅ የተሠጣቸውና የሠሌዳ ቁጥሩ መከ ኮድ 2-2347 የሆነ ኦራል ተሽከርካሪን በመጠቀም ነው ፡፡

ሰዎቹን በመጓጓዝ ላይ እንዳሉ የተያዙትም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሌ ዞን ቀርቀርቴ በተባለ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነው ፡፡ ተከሳሾቹ በፎቶ ፣ በሰነድ አና በሰው ምስክር የቀረበባቸውን ክስ ሊያሰተባብሉ አልቻሉም ፡፡

የሐዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ የዞኑን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ጠቅሶ እንደዘገበው ፍርድ ቤቱ እያንዳንዳቸው በ8 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት እና እንዲሁም በ10,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ተወስኗል ፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ተፅዕኖ ፈጣሪዎች” የተባሉ ግለሰቦች በምክክሩ እንዲሳተፉ በምን መስፈረት ተመረጡ?

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 17ኛ ቀን ውሎ የክልል ተወካዮች ጉባኤ...

የአሜሪካ ጦር እስራኤልን ከኢራን መከላከሌን ላቆም እችላለሁ አለ

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በናረበት በዚህ...

በፌደራሉ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ

ከሱዳን ጋር በሚዋሰነው የሰሜናዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ በሚገኝ...

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...