ከ11 ሺህ በላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቃላትን ይዟል
የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላትን በአማርኛና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች የያዘ መጽሐፍ ተመርቋል።
በመዝገበ ቃላቱ የመጀመሪያው ዕትም ከ11 ሺህ በላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቃላት አቻ ስያሜ ለመስጠት ጥረት መደረጉ ተነግሯል፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዚዳንት ፕ/ር በላይ ካሳ እንዲሁም ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዶ/ር በለጠ ሞላ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ መጽሐፉ በየጊዜው እያደገና እየተሻሻለ የሚሄድ ዘመን ተሻጋሪ ሥራ ነው።
ሳይንሳዊ እውቀትን በሀገር ውስጥ ቋንቋ በመተርጎም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ተናግረዋል፡፡
