የቅድስት ቤተክርስቲያንን ጥቅምና ክብር በማስጠበቅ ሁሉም ተቋማት ሕግንና መመሪያን ጠብቀው እንዲሠሩ  ተወሰነ

Date:

                                                                                                                                    
                                                                                                                                                                                                                                                                               
አጀንዳ ቁጥር ፯  በስፋት ተወያይቶ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏል።                                                                                                     በዩኒቨርሲቲው መዋቅራዊ አስተዳደር መሠረት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርም ሆነ የጽ/ቤቱ አጠቃላይ ሥራ ተጠሪነቱ ለዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ እንደመሆኑ መጠን  ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ የሥራ ዕቅዱን ለሥራ አመራር ቦርድ አቅርቦ በማስገምገም ካጸደቀ በኋላ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አቅርቦ ሲፈቀድ ወደ ትግበራ መግባት ሲገባው የሥራ አመራር ቦርዱም ሆነ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ባላጸደቀው ፕሮጀክት በቋሚ ሲኖዶስም ሆነ በምልዓተ ጉባኤ ሳይፈቀድለት ከፍተኛ ብድር መበደሩ ተገቢ ስላልሆነ ዩኒቨርሲቲው ከዓባይ ባንክ አክስዮን ማኅበር ጋር የገባው የብድር ውል ስምምነት እንዲቋረጥ፤

  1. ዩኒቨርሲቲው ከዓባይ ባንክ አክስዮን ማኅበር ጋር በገባው የውል ስምምነት መሠረት በመጀመሪያ ዙር የወሰደውን ብድር ብር 166‚045‚410.91 (አንድ መቶ ስልሳ ስድስት ሚሊዮን አርባ አምስት ሺህ አራት መቶ ዐሥር ብር ከዘጠና አንድ ሣንቲም) በአጭር ጊዜ ውስጥ ተመላሽ አድርጎ በብድር ማስያዣነት ያስያዛቸውን የሁለቱንም ሕንጻዎች እግድ በማስነሳት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታዎችን በመረከብ ተመላሽ እንዲያደርግ፤
  2. ዩኒቨርሲቲው ተጨማሪ ሕንጻ መገንባቱ የሚደገፍና ለዩኒቨርሲቲው ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ በመሆኑ የጀመረውን የማስፋፊያ ሕንጻ ግንባታ ከውስጥ ገቢው ላይ በጀት በመመደብ ግንባታውን እንዲያስቀጠል፤
  3. በቀጣይ አዋጭ የሆነ ፕሮጀክት ለማልማት የአዋጭነት ጥናት እንደገና በተገቢው ሁኔታ ማጥናትና ለምን ዓይነት አገልግሎት እና ምን ያህል ስፋት ወይም ወለል ያለው ሕንጻ ቢሠራ አዋጭ ይሆናል? የተጀመረው ሕንጻ  እንዴት መጠቀም ይቻላል? የሚለውን መለየትና ማጥናት ስለሚገባ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ገለልተኛ አጥኚ የባለሙያ ኮሚቴ ተቋቁሞ ተጠንቶ በቋሚ ሲኖዶስ እየታየ ተግባር ላይ እንዲውል፤
  4. በየደረጃው ያሉ የቤተክርስቲያኒቱ ተቋማት የቤተክርስቲያናችንን አንጡራ ሀብት ሕንጻዎችን፣ መሬቶችንና ሌሎች ቋሚ ንብረቶችን በማስያዝ መበደሩ ከቀጠለ በዋስትና የተያዙ ቋሚ ንብረቶቿ እየተሸጡ ቋሚ ንብረት አልባ ስለሚያደርጋት በቀጣይ ያልተገቡ ብድሮችን ማስቆም እንዲቻል በየደረጃው ያሉ በጠቅላይ ጽ/ቤት ሥር የሚገኙ ድርጅቶችና የትምህርት ተቋማት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታዎች በማዕከል ደረጃ በጠቅላይ ጽ/ቤት ተደራጅተው እንዲቀመጡ ሆኖ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሳያውቀው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሳይወሰንና ሳይፈቀድ የትኛውንም ቋሚ ንብረት በማስያዝ ብድር መበደር እንዲቆም ለሁሉም አህጉረ ስብከት መመሪያ እንዲተላለፍ ይደረግ በማለት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕንጻ መሠረት ድንጋይ ጥር 4/2016 ዓ/ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት  ቡራኬ እንደተቀመጠ የሚታወስ ነው።

ዘገባው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...