በአዲስ አበባ ከተማ ትምባሆ በተቋማት እና ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ላይ መጠቀም እና ማጨስ የተከለከለ ሲሆን ለዚህም 23ሺህ451 ተቋማት ላይ የቁጥጥር ስራ ለማከናወን ታቅዶ በ25ሺህ485 ተቋማት ላይ ቁጥጥር መደረጉ ተገልፆል፡፡
በተደረገ ቁጥጥር የትንባሆ ክልከላ የተላለፉ 54 ተቋማት ከ128ሺህ ብር በላይ የተቀጡ ሲሆን የትምባሆ ህግ የመተላለፍ ችግር የተኘባቸው ተቋማት የማስተካከያ እርምጃ የተወሰደባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የምግብና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ተናግረዋል።
ትምባሆ ማጨስ የተከለከለባቸው እና ቁጥጥር የሚደረግባቸው የህዝብ መገልገያና መሰብሰቢያ ስፍራዎች እና የተከለከለ ቦታ ላይ ትምባሆ መጠቀም እና ማጨስ ያሉባቸዉ ተቋማት ላይ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን ከ28 ሺህ ፓኮ በላይ የትንባሆ ምርቶች ተወግዷል።
ትምባሆ የሚያስከትለው ጉዳት ለመቀነስና ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎች እየወሰደ ቢሆንም የትምባሆ ኢንዱስትሪው ምርቶችን አጓጊ ለማድረግና የገበያ ፍላጎቶት እንዲጨምር ለማድረግ የተለያዩ ስልቶችን ነድፎ እየሰራ በመሆኑ ማህበረሰቡ ይህን ድርጊት ተረድቶ እራሱንና ቤተሰቡን ከትንባሆ ጭስ ሊከላከል ይገባል ተብሏል፡፡
በመሆኑም በቀጣይ በተለያዩ ተቋማት ላይ የሚደረገው ቁጥጥር እና እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ጨምረው ተናግረዋል።
ለብስራት ሬዲዮ
