የቻይናው J-10 የአለም መነጋገሪያ ሆኗል

Date:

ፓኪስታን ይህንን ጄት በመጠቀም ነው አምስቱንም የህንድ ዘመናዊ ጦርጄቶችን እንድሁም 12 ድሮኖችን አየር ላይ ያስቀረቻቼው።

ሌላው የሚደንቀው ነገር እነዚህን የህንድ ጦር ጄቶች ለመምታት ፓኪስታን የወሰደባት ጊዜ የተወሰኑ ደቂቃዎች ብቻ መሆናቸው ነው።

በቻይና ሰራሹ J-10 ተጠቅማም የከሰከሰቻቼው የህንድ ጦር ጄቶች ዋጋቸው አንድ ቢሊዮን ዶላር ያወጣል። በተለይም ፈረንሳይ ሰራሹ ራፋይል ለህንድ እንዲሆን ተደርጎ ለመሰራት ህንድ በእያንዳንዱ የጦር ጄት ላይ ከ 250 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርጋበታለች።

የህንድ ሶስት ራፋይል አንድ ሚግ እና አንድ SU-30 አይሮፕላኖችን መቶ የጣለው የቻይናው ቼንግዱ J-20 ታዲያ ለቻይና ኩራት ሆኗታል። ቻይናም ክስተቱን እንደ መባረክ ቆጥራዋለች።

የቻይናን ጦር ጄቶች ይህን ብቃት ማሳየታቸውን ተከትሎ የቻይና የጦር አክሲዮን ገበያ እስከ 20% አሻቅቧል። ቻይና የጦር ጄቶቿን ለአለም የጦር ገበያ ብዙም ያላቀረበችና ካላት የጦር አቅም አንፃር የመሳሪያ ሽያጯ አነስተኛ ቢሆንም አሁን አሁን ላይ የምታመርታቼው የጦር ጄቶች ከሁሉም የአለማችን ዘመናዊ ጦር ጄቶች በቴክኖሎጂ ረቂቅነታቸው ቀድመው ሄደዋል።

J-10 ም ፈረንሳይ አሉኝ ከምትላቸው የ 4.5 ጄኔሬሽን ጦር ጄቶች ጋር አየር በአየር ተፋልሞ እንደ ቀላል መጣል መቻሉ አስገራሚ ሆኗል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...