የ14 ዓመቷን ልጃገረድ ደፍረው በአሰቃቂ ሁኔታ ወደ ገደል ወርወረው የገደሉ ወንጀለኞች በእድሜ ልክ እስራት ተቀጡ

Date:

አሰቃቂ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ፅምብላ ወረዳ ለምለም ቀበሌ ገበሬ ማህበር ዓዲ እራር መንደር መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ.ም ነው።

ያይንሸት ገብረዋህድ እመሃ የተባለው የ35 ዓመት ጎልማሳ የተጠቀሰው አከባቢ ተወላጅ ነው።

መጠጥ በመሸጥ የምትተዳደርን እና አሁን አብራው ያልሆነችውን የልጁን እናት ” አብረን ለማደር ጥይቄሽ እምቢ ብለሽኛል ” የሚል  ቂም ይቋጥራል። 

ግለሰቡ ቂሙን ለመወጣት ሆን ብሎ በማሰብና በመዘጋጀት የምትኖርበት ቤት መኝታ ክፍል አዘናግቶ ገብቶ ከአልጋ ስር ይደበቃል።

እናት ስራዋን ጨርሻ አገር አማን ብላ መተኛቷን አረጋግጦ ከሌሊቱ 5 ሰዓት ከተደበቀበት በመውጣት በመጥረብያ ደጋግሞ ቢመታትም ህይወቷ ሳያልፍ ትተርፋለች።

ፓሊስ ወንጀለኛውን ያይንሸት ገብረዋህድ ይዞ በእናቲቱ ላይ የፈፀመውን ድርጊት አጣርቶ በፍርድ ቤት ግድያ ሙከራ ክስ ይመሰርትበታል።

በኃላም በዋስ ይለቀቅና ጉዳዩንም ከውጭ ሆኖ መከታተል ይጀምሯል።

ይህ በእንዲህ እያለ ብቸኛ ምስክር ትሆናለች ብሎ ያሰባትን እናቲቱ ከሌላ የወለደቻትን የ14 ዓመቷን ልጃገረድ ከጓደኛው ጋር በመሆን አታልለው ወደ ገደላማ ቦታ በመውሰድ በቡድን ደፍረው ሲያበቁ ወደ ገደል ወርውረው በግፍ ገድለዋታል።

የተፈጸመው የወንጀል ተግባር ውስብስብ ያለና ማስረጃ ለማጥፋትና ለመሰወር ሆን ተብሎ መሰራቱ  የማጣራት ሂደቱ የተወሳሰበና ዘለግ ያለ ጊዜ እንዲወሰድ ምክንያት ሆኗል።

የዞኑ ማእከላይ ፍ/ቤት ወንጀለኞቹ  በኢ/ፌ/ዲ/ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 539 (1) (ሐ) መሰረት በዕድሜ ልክ እስራት መቅጣቱ አስታውቀዋል። 

መረጃው ከድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን የተወሰደ ነው። 

@tikvahethiopia            

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጥቃት አድራሹ ከካሊፎርኒያ መሆኑን ትራፕ ገለፁ

ትናንት ቅዳሜ ምሽት በዋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማኅበር የእራት ግብዣ...

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...