በባህል ድምፃዊነቱ አራት አስርት ዓመታትን ያስቆጠረው ዝነኛው ድምፃዊ የጥብበ እና ህይወት ጉዞው የሚዳሰስበትን መፅሀፍ ማጠናቀቁን አሳውቋል::
ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 መሰንበቻ ፕሮግራም ጋር ቆይታ ያደረገው ድምፃዊ ይሁኔ በላይ “ፍኖተ ጥበብ” የሚል ርዕስ የሰጠው መፅሀፉ በቅርብ ቀን ለአንባቢ እንደሚቀርብ ተናግሯል።
«በመፅሀፉ ከተወለድኩበት ፍኖተ ሰላም እስከ አሜሪካ እንዲሁም በሙዚቃ ህይወቴ እና ኑሮዬ ያሳለፍኩት ጉዞ የሚተረክበት ነው።»
ይሁኔ በላይ ለመፅሀፉ ዝግጅት በተለያዩ ጊዜያት በስራ ላይ እያለም ፅፎ ያስቀመጣቸው ማስታወሻዎቹ መነሻ እንደሆኑት ግልፆ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጊዜ ሀሳቡን ወደ መፅሀፍ አሳድጎ ወጥ በሆነ መንገድ ለማቅረብ ሲዘጋጅ እንደነበር ተናግሯል::
ለንባብ ቅርብ መሆኑን ባለው ክፍተት ሁሉ እንደሚያነብ እና ለፅሁፉ ልምድ እንደሰጠው ገልፆ “ፍኖተ ጥበብ” የተሰኘው መፅሀፉ በተደራጀ መንገድ እንዲሁም ስነ ፅሁፋዊ ለዛ ባለው ሁኔታ እንዲቀርብ ግን ደራሲ አቤል ጋሼ እና መጋቢ ጥበባት አበረ አዳሙ በአርትኦት ስራ እንደረዱት ተናግሮ አመስግኗቸዋል::
መፅሀፉ በቅርቡ በኢትዮጵያ እንዲሁም
ሰኔ 21/2025 በአሜሪካ የሙያ ባልደረቦቹ በተገኙበት እንደሚመረቅ ተናግሯል::
ይሁኔ ከመፅሀፉ በኃላ አዲስ አልበሙን ለአድማጭ እንደሚያቀርብም ገልፆል::
«ዕውቅና ድንቅ ሙያተኞች በዜማ እና ግጥም አበበ ብርሀኔ: ተዘራ ተችሎ ፀጋዬ ደቦጭ: ተስፋ ብርሀን እና አንተነህ ይግዛው በሙዚቃ ቅንብሩ ሄኖክ ነጋሽ ሲገኝ ዳዊት ጥላሁን አንድ ሙዚቃ አቀናብሮልኛ»
ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1
