የአሜሪካ ኤምባሲ ጎንደር ዩኒቨርሲቲን በይፋ አመሰገነ

Date:

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ፣ በአጼ ቴዎድሮስ ካምፓስ የሚገኘውን ዋና ቤተመጻሕፍት በአሜሪካው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሃሪ ትሩማን ስም በመሰየሙ በይፋ አመስግኗል፡፡

“የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአጼ ቴዎድሮስ ካምፓስ የሚገኘውን ዋና ቤተ መፃህፍት “የትሩማን ቤተ መፃህፍት” ብሎ በመሰየም ፕሬዚዳንት ሃሪ ትሩማንን በመዘከሩ እናመሰግናለን።” ብሏል የአሜሪካ ኤምባሲ፡፡

ኤምባሲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው የምስጋና ቃል፤ “ይህ ክብር እ.ኤ.አ በ1954 የጎንደር የማህበረሰብ ጤና ኮሌጅና የማሰልጠኛ ማዕከልን (የአሁኑ ታዋቂው የጎንደር ዩኒቨርሲቲን) ለመመስረት የረዳውን የፖይንት ፎር ዓለማቀፍ የትብብር መርሃ ግብር በማስጀመር ረገድ ፕሬዚዳንት ትሩማን ለተጫወቱት ወሳኝ ሚና እውቅና የሚሰጥ ነው” ብሏል፡፡

ዕውቅናው የዩኒቨርሲቲው 70ኛ ዓመት የምስረታ በዓልና የማስተማሪያ ሆስፒታሉ 100ኛ ዓመት የምስረታ በአል ላይ ይፋ መደረጉን የጠቀሰው ኤምባሲው፤ ይህ ምዕራፍ በአሜሪካና በኢትዮጵያ መካከል በትምህርት፣ በማሕበረሰብ ጤናና በማህበረሰብ ልማት ያለውን ዘላቂ ትብብር እንደሚያሳይ ጠቁሟል፡፡

በመጨረሻም፤ “ይህንን የጋራ ታሪክ በመዘከራችን ኩራት ይሰማናል፤ እናም ይህን ተጽዕኖ ፈጣሪ አጋርነት ለመቀጠል በጉጉት እንጠብቃለን!” ብሏል።(አ.አ.ኦ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

መረጃ በማይሰጡ ኃላፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የሚያስችል ሕግ ተዘጋጀ

የመገናኛ ብዙሃን እና የመረጃ ነፃነት የየራሳቸው ባህሪ ቢኖራቸውም እስካሁን...

የ30 ዓመታትን ጉዞ የሚዘክረው ዳሸን ኤክስፖ

የዳሸን ባንክን 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው...

‹‹ሀገር ጥለው የጠፉና ድርጅቶቻቸውን ለመዝጋት የተገደዱ አሉ››

አቶ አለማየሁ ከተማ(የኢትዮጵያ ሪልስቴት አልሚዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት) ግዮን መጽሔት :-...

የሰላም ስምምነት ሳይፈጸም የንግድ መርከቦች ጉዞ እንደማይጀምሩ የነዳጅ ጫኝ ኩባንያ ኃላፊ ተናገሩ

የሲውዲን ነዳጅ አጓጓዥ ኩባንያ የሆነው ‘ስቴና በልክ’ ዋና ስራ...