የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም

Date:



የጥንት ኢትዮጵያዊያንአርበኞች ድል 85 ኛው ዓመት መታሰቢያ ሚያዚያ 27 ኢትዮጵያውያን የፋሽስት ወረራን በሕብረትና በአርበኝነት ተጋድሎ የቀለበሱበት ቀን ነው። ይህ ድል ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ ውድመት፣ እልቂት ከደረሰ እና መስዋዕትነት ከተከፈለ በኋላ የተገኘ ሲገኝ፣ የወቅቱ ሕዝብ አንድነት ለድሉ ጉልህ ሚና እንደነበረው ይታመናል። ለመሆኑ ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት ይህንን ድል መሸከም የሚችልና አንድነትን የሚያጎላ ትውልድ አላት?


ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም ኢትዮጵያን ለአምስት ዓመታት ወርሮ የቆየው የፋሽስት ጣልያን ኃይል ተሸንፎ የወጣበት ቀን ነው። በወቅቱ በነበሩ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ብርቱ ተጋድሎ የተገኘው ይህ የድል ቀን ዛሬ 85 ዓመት ሞላዉ።


ይህ የኢትዮጵያዊያን ድል ሁለተኛው የዓለም ጦትነት በአፍሪካ ምድር የማብቃቱ ዕውነት ማሳያ ጭምር ነበር። በዚያን ጊዜ ኢትዮጵያ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የአንድነቱ ጎራ አባል በነበረችው እንግሊዝ ድጋፍ ጭምር ነው ይህን ድል የተቀዳጀችው።


ርእሠ ብሔር ታዬ አፅቀ ሥላሴ መሃል አዲስ አበባ አራት ኪሎ የአርበኞችሐውልት በቆመበት ድላችን ሐውልት ላይ ባደረጉት ንግግር “የምናከብረው የድል እንጂ የነፃነት ቀንን አይደለም” ብለዋል። እንዲህ ያለው መልእክት በሚተላለፍባት የዛሬዋ ኢትዮጵያ ግን አንድም ጎሳን፣ በሌላ በኩል ሃይማኖትን እና ታሪክን መነሻ ያደረጉ እኛ እና እነሱ የሚሉ ሽኩቻዎች ይታያሉ። 


እነዚህ እውነታዎች የግጭትም፣ የጥቃትም መነሻ ሆነው ሰው ሲገደልባቸው፣ ከኖረበት ሲፈናቀልባቸው ይታያል። በመሰረታዊ ጉዳዮች መግባባት እያቃተም ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞላት ምክክር ላይ ትገኛለች። ያነጋገርናቸው ሰዎችም ለነዚህ ሐቆች አብነት ናቸው።


የኢትዮጵያ ርእሠ መስተዳድር ወይም ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ይህንን የድል ቀን አስመልክተው በጽሑፍ ባጋሩት መልዕክት፣ “ሚያዝያ 27 ቀን ኢትዮጵያውያን ጀግኖች አርበኞች የፋሽስትን ወረራ የቀለበሱበትና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ ያስከበሩበት በዓል ነው” ሲሉ ጽፈዋል። አክለውም ለአርበኝነትበሰጡት ብያኔ “ከራስ ወዳድነት የነጻ መሥዋዕትነት” መሆኑን ጠቅሰው፣ “አርበኝነት የራስን ጥቅም ለሀገር ጥቅም ሲባል መተው፣ የግል ክብርን፣ የግል ሥልጣንን እና የግል ጥቅምን መሠዋት ነው” ብለዋል።


ለመሆኑ ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት ይህንን ድልም ሆነው በሕብረት የተገኘውን ነጻነትን የማስጠበቅ ተጋድሎ መሸከም የሚችልና አንድነትን የሚያጎላ ትውልድ አላትን? የናዚ ጀርመኑ ቁልፍ አጋር የነበረችው ፋሽስት ጣልያን ምንም እንኳን ኢትዮጵያውያን በአድዋ ድል ያደረሱባትን ከባድ ሽንፈት መበቀል አላማ ብታደርግም፣ የአምስት አመቱ ወረራው አለም ላይ ወደር የሌለው እልቂትና ውድመት ያደረሰው የሁለተኛው የዓለም ጦርነት አካል ነው።

DW

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...