የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት 27ተኛውን አለማቀፍ አዲስ ቻምበር የንግድ ትርኢት ማካሄድ ጀመረ፡፡
ይህ የንግድ ትርኢት የሀገር ውስጥ የንግዱ ማህበረሰብ ከሌሎች ሀገራት አቻቸው ጋር የገብያ ትስስር እንዲፈጥሩ እድል እያመቻቸ ነው ተብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሃራ መሃመድ ከዚህ ቀደም የተዘጋጁ የንግድ ትርኢቶች የንግዱ ማህበረሰብ ያለው የገብያ ትስስር እንዲሰፋ አድርጓል ብለዋል፡፡
የንግዱ ዘርፍ ከተማ ውስጥ እንዲሰፋ ለማድረግ ምክር ቤቱ ላለፉት 10 አመታት ዋንኛ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ነው ያሉ ሲሆን ሀገሪቱ ከአለማቀፍ ንግድ አቀላጣፊ ማህበራት ጋር ያላት ግንኙነት የተሻለ እንዲሆን የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ ነው ይላሉ፡፡
በየአመቱ በሚዘጋጀው አለማቀፍ አዲስ ቻምበር ንግድ ትርኢት ላይ ከሌሎች ሀገራት የንግዱ ማህበረሰብ ጋር የገብያ ትስስሮች እንዲፈጠሩ ጥረቶች እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ ከተማ አስተዳደሩ የንግድ ስርዓቱን ለማስተካከል እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አሁን እየተደረጉ ያሉ ስራዎች ላይ ሁሉም የንግድ ስራዎች በእኩል እንዲስተናገዱና የተሻለ እድገት እንዲያስመዘግቡ ለማድረግ እየሰራን ነው በማለት አስረድተዋል፡፡
ነገር ግን የንግዱ ማህበረሰብ ስራዎቹን ዘላቂ መሆን አለበት በየጊዜው የሚታዩ ችግሮችን ሰበብ በማድረግ ህገወጥ አካሄድን ለመከተል መንቀሳቀስን መከላከል አለበት ሲሉም መክረዋል፡፡
በ27ተኛው አዲስ ቻምበር አለማቀፍ የንግድ ትርኢት ላይ ወደ 80 የሚሆኑ ተቋማት የተሳተፉ ሲሆን ከቻይና ህንድንና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ልኡካን በትርኢቱ እየተሳተፉ ነው፡፡
የንግድ ትርኢቱ እስክ ሚያዝያ 17 ድረስ እንደሚዘልቅም ተነግሯል፡፡
የአዲስ አበባ ቻምበር የንግድ ትርኢት ማካሄድ ጀመረ
Date:
