ከ2028 ጀምሮ የአፍሪካ ዋንጫ አሁን እየተካሄደበት ያለውን ፎርም በመቀየር በየአራት ዓመቱ እንደሚካሄድ የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞሴፔ አስታወቁ።
ይሄ ውሳኔ የተላለፈው ዛሬ በሞሮኮ ራባት በተደረገው የካፍ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ ነው።
የአፍሪካ ዋንጫ ከ1968 ጀምሮ በየሁለት ዓመቱ ሲካሄድ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፥በ2012 እና 2013 ብቻ በአንድ ዓመት ልዩነት ተካሂዷል።
የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ በሶስቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት (ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ) የጋራ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።
ከቀጣዩ ዓመት (2028) አንስቶ ግን በየአራት ዓመቱ መካሄድ ይጀምራል።
ከ2029 አንስቶ ደግሞ ልክ እንደ አውሮፓው ሁሉ የአፍሪካ ኔሽንስ ሊግ ዋንጫ እንደሚጀመርና በየዓመቱ እንደሚካሄድም የካፍ ፕሬዝዳንት ሞሴፔ አስታውቀዋል።
ምስጋናው ታደሰ
