የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የንግድ ምልክትና የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ምዝገባ አገልግሎቶችን ለማዘመን የኤሌክትሮኒክ (e -service) አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት እና ኮምኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ለብስራት ሬዲዮ ጨምረው ገልፀዋል።
የተገልጋይ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የገለፁት አቶ ኤልያስ የአገልግሎት ተደራሽነቱን ለማስፋት እና ዘመኑን ያማከለ አሰራር ለመዘርጋት የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት መጀመሩ በእጅጉ ያግዛል ብለዋል።በተለይም ሃገሪቷ የጀመረችውን የዲጅታል ኢኮኖሚ እውን ለማድረግ እንደተቋም የሚያበረክተው ሚና እንዳለ ገልፀዋል ።
የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ያለውን ሰፊ አገልግሎቶች ዘመናዊ ለማድረግና ተገልጋዮቹን የበለጠ ለማርካት አለም አሁን ያለችበትን የዲጅታል ዘመን ባማከለ መንገድ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስፈልግ ገልፀው ተጨማሪ ስልጠናዎች እንዲሁም ሌሎች የድጋፍ ስራዎችም መስራት እንደሚያስፈልግም አቶ ኤሊያስ መሀመድ ተናግረዋል፡፡
