የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ውስጥ በረራ 28 ሚልዮን ዶላር መክሰሩን አስታወቀ

Date:

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሀገር ውስጥ በረራ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው በኪሳራ እንደሆነ እና ማትረፍ አለመጀመሩን አስታውቋል።

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው: ተቋሙ ባለፈው ዓመት በሀገር ውስጥ በረራ ምክንያት 28 ሚሊየን ዶላር ኪሳራ ማስተናገዱን ተናግረዋል።

ኪሳራው ያጋጠመው በቅርቡ በተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ምክንያት በውጭ ምንዛሬ ገበያ ላይ ለታየው ለውጥ ተመጣጣኝ የሆነ የዋጋ ጭማሪ በሀገር ውስጥ በረራዎች ላይ ባለመደረጉ ነው ተብሏል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው የ2018 ዓ.ም. የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸምን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ አየር መንገዱ አሁንም ትርፍ ማግኘት ባይቻልም በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ 6 ወራት የኪሳራው መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን አብራርተዋል።

ተቋሙ በሀገር ውስጥ በረራዎች እያጋጠመው የሚገኘውን ኪሳራ ቀስ በቀስ ለማስወገድ በበረራ ትኬቶች ላይ ደረጃ በደረጃ የዋጋ ማስተካከያዎች እያደረገ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...