የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2024 “የቢዝነስ ትራቭለርስ አዋርድስ” የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ሽልማትን አግኝቷል።
አየር መንገዱ ሽልማቱን ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ ማግኘቱን አስታውቋል።
የአየር መንገዱ ደንበኞች እያደረጉት ላለው ድጋፍ ምስጋናውን አቅርቧል።
“ቢዝነስ ትራቭለርስ አዋርድስ” የ“ቢዝነስ ትራቭለርስ” መጽሔት አንባቢዎች በሚሰጡት ድምጽ አሸናፊው የሚለይበት የአቪዬሽን ሽልማት አይነት ነው።
