እስከ 20 በመቶ ሀገራዊ የኢኮኖሚ አስተዋፅኦ እንዳለው የሚነገርለት የግንባታው ዘርፍ በብልሹ አሰራርና በደህንነት ችግሮች በተደጋጋሚ ቅሬታ የሚቀርብበት ዘርፍ ነው።
በግንባታው ዘርፍ የሚስተዋሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለለት ሶፍትዌር በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን እና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ትብብር ለምቶ ይፋ ተደርጓል።
አዲሱ የግንባታ ቁጥጥር መረጃ ሶፍትዌር (CRIS) በተበታተነ ሁኔታና በሰው ኃይል ይከናወኑ የነበሩ ስራዎችን የተናበበ፣ የተዋሃደ ብሎም በመላ ሀገሪቱ የሚካሄዱ የግንባታ ቁጥጥር ሂደቶችን ወጥ ወደሆነ የዲጂታል አስተዳደር ለማዋሃድ እንደሚያስችል ተገልጿል።
ስርዓቱ የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን በመቆጣጠር ደህንነታቸው የተጠበቀ ብሎም ግንባታዎች ከተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እና ከተመደበላቸው በጀት ባነሰ ሁኔታ ውጤታማ ሆነው እንዲከናወኑ የላቀ አበርክቶ እንዳለው ተመላክቷል።
NBC Ethiopia
