- ደጃች ውቤ (ውቤ በረሃ) የአራዶች መዝናኛ፣ የአራዶች መገናኛ ብለው እነደራሲ ስብሃት ገ/እግዚአብሔር ጽፈውለታል።
አፍንጮ በርን በወደ ቅድስት ማርያም መንገድ ሻገር እንዳሉ አንድ ስመጥር ሆቴል አለ። ብዙዎች ኤፍሬም ውስኪ በሚል መጠሪያ ያውቱቁታል።
ከደጃች ውቤ በልማት ሲፈርስ ከቦታው ብዙ ላለመራቅ አፍንጮ በር አካባቢን የግለሰብ ቤት ተከራይቶ መስራቱን ቀጠለ። ይህ የቅርብ ዐመት ታሪኩ ነው።
እያደር ቁልፍ ገዝቶ ስራውን ቀጠለ። ምግብም መጠጥም በጥራት ስለሚያቀርብ የደንበኞቹ ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ሄደ። መጨመር ብቻም አይደለም ደንበኞቹ የዛሬ 20 ዓመት በጠባቧ ቤት በትንሽ ወምበርና ጠረጴዛ አብረው የነበሩ ታማኝ ደንበኞች ናቸው ዛሬ ሆቴሉ አድጎ ኤፍቢ ሆቴል ተብሎ ዘመናዊ የሆነውን ላውንጅ ለማስመረቅ በቅቷል።
አቶ ኤፍሬም በለጠ፣ የሥራ ፈጠራ ጉዟቸው የጀመሩበትን 20ኛ ዓመትን በማስመልከት አዲሱን ባለሦስት ኮከብ ሆቴላቸውን እና ዘጠነኛ ፎቅ ላይ የሚገኘውን ዘመናዊ ላውንጅ አስመርቋል።
ባለ 12 ፎቅ ሕንፃ፣ ለበርካታ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠሩ የተገለጸ ሲሆን፣ የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱም ባለቤቱ ከግል ተቀጣሪነት ወጥተው የራሳቸውን የንግድ ፈቃድ ያወጡበትን ዕለት ለማስታወስ የተዘጋጀ መርሃ ግብርም ነው ብለውናል አቶ ኤፍሬም።
ባለሦስት ኮከብ ሆቴል፣ 24 ዘመናዊ የመኝታ ክፍሎች ያሉት፣ የስፖርት ማዕከል፣ የስቲም ሳውና፣ ሬስቶራንት፣ ባር እና ማራኪ ዕይታ ያለው ዘመናዊ ላውንጅ አካቶ የያዘ ሲሆን ለ62 የአገር ውስጥ ሠራተኞች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል።
ከ32 ዓመታት በፊት በሌላ ሰው ቤት ውስጥ በጽዳትና በብርጭቆ ማጠብ ሥራ ሕይወታቸውን እንደጀመሩ የገለጹት አቶ ኤፍሬም፣ ከዚያም በኪራይና ቀስ በቀስ ሱቆችን በመግዛት ወደ ግል ሥራ መሸጋገራቸውን ነግረውናል።
አዲስ አበባ ስትነሳ አራዳ አካባቢና ደጃች ውቤ አብረው ይነሳሉ። በጽሁፍም በሙዚቃም ስለእነዚህ ቦታዎች ብዙ ተብሏል። ያኔ በደጃች ውቤ በትንሽ የተጀመረው ዛሬ ትልቅ ሆቴል ሆኗል።
የምስጋና መርሃ ግብርና የሆቴሉን ተጨማሪ አገልግሎት ለመመረቅ በተከናወነው ፕሮግራም ላይ በርካታ ህዝብ ታድሟል። ሁሉም ታዳሚ ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ወዳጅና ደንበኛ ከመባል አልፈው ቤተሰብ የሆኑ የተሰባሰቡበት ምሽት ነበር።
አገልግሎቱ ላይ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግ በስፋት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ነው መስራቹ አቶ ኤፍሬም የነገሩን
