የዛሬው ኀዘናችን የነገው የትንሣኤያችን መሠረት ነው

Date:

“እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን፤ የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ” (ራእይ ፪፥፲)

በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤ እና በሙኔሳ ወረዳዎች በክርስቶስ ክቡር ደም በተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ በደረሰው አስከፊ ጥቃት፣ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን በግፍ በተሠዉበት እና አብያተ ክርስቲያናት በወደሙበት አሳዛኝ ክስተት በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ እና በደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ስም የተሰማንን እጅግ መሪር ኀዘን እንገልጻለን።

የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አርአያ የተፈጠረ፣ ክብሩም ከሁሉ በላይ የሆነ ነው። በአርሲ ምድር የተፈጸመው ግፍ፣ የሰብአዊነትን ክብር የተጋፋና የሰላምን ተስፋ ያጨለመ ነው።

ነገር ግን እኛ ክርስቲያኖች በመከራ ውስጥ እንኳን ተስፋ የምንቆርጥ አይደለንም። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን፣ ፈተናው የቱንም ያህል ቢከብድ ለጽድቅና ለእምነት የሚከፈለው ዋጋ በሰማይ የሚያሰጠው ክብር ታላቅ ነው።

የዛሬው ኀዘናችን የነገው የትንሣኤያችን መሠረት ነው። በግፍ የተሠዉ ወገኖቻችን እንደ መጀመሪያዎቹ ሰማዕታት የሕይወትን አክሊል እንደሚቀዳጁ ሙሉ እምነታችን ነው።

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት፣ ቤተ ክርስቲያናችን ለዘመናት ጸንታ የቆየችው በደም ሳይሆን በምሕረት፣ በክፋት ሳይሆን በይቅርታ መሆኑን አምነን፣ ምእመናን በዚህ ፈተና ውስጥ እንደ አለት የጸና እምነት እንዲኖራቸው አጥብቀን እናሳስባለን።

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት በዚህ የፈተና ወቅት ከተጎዱ ወገኖች፣ ከቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምእመናን ጎን በመቆም፣ የጸሎትና የሞራል ድጋፋቸውን ያደርጋሉ። በኃይል የሚመጣ ጥቃት ጊዜያዊ ነው፤ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ግን እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ጸንታ ትኖራለች።

አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ለተጎዱት ቤተሰቦች መጽናናትን ይስጥልን፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይጠብቅልን።

ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት፣ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ለተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች የሚጫወቱ ወንድማማቾች

የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ተጫዋቾችን...

ኢንፊኒቲ ለቤትና ለመኪና መግዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ...

የአዲሱ የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት የእርማት ስራዎች ሳይጠናቀቁ በሥራ ላይ እየዋለ ነው

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት...

ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ

​የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ለመጀመሪያ...