የዳኞች ማኅበር በጸጥታ ችግር ምክንያት ዓመታዊ ግምገማ ማካሔድ አልቻልንም

Date:

የአማራ ክልል የዳኞች ማኅበር በጸጥታ ችግር እና በትራንስፖርት እጥረት ምክንያት የ2018 በጀት ዓመት ሪፖርት እና ግምገማ ማካሄድ እንዳልቻለ አስታውቋል።

እንደ ማኅበሩ ገለጻ፤ በክልሉ ያለው የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ ባለመሆኑ አባላቱን ከ14ቱም ዞኖች ሰብስቦ በዋና ጽህፈት ቤቱ ባህር ዳር ከተማ ማገናኘት አልቻለም።

የማኅበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ብርሃኑ አሰፋ፣ “የማኅበሩ የ6 እና የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶች እስካሁን አልተገመገሙም” ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ማኅበሩ የዘንድሮውን በጀት ዓመት የሥራ እንቅስቃሴ አለመገምገሙ በአባላቱ ላይ የደረሰ ጉዳት መኖር አለመኖሩን እንዳይረዳ እንቅፋት ሆኖበታል ተብሏል።

በቀጣይ በክልሉ የሚኖረውን የጸጥታ ሁኔታ በመመልከት አስቻይ ሁኔታ ከተፈጠረ በ2019 በጀት ዓመት መስከረም የአፈጻጸም ሪፖርት ለማቅረብ እና አጠቃላይ ግምገማ ለማካሔድ ዕቅድ መያዙን የማኅበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ብርሃኑ ገልጸዋል።

ማኅበሩ የአባላቱን ደህንነት ለማስጠበቅ ገለልተኛ በሆነ እና ሕጋዊ አሰራርን በተከተለ መንገድ ለመስራት እየጣረ እንደሆነ ኃላፊው አስረድተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...