የግል አልሚዎች እንዲሳተፉ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል

Date:

በዘርፉ ያለውን የኃይል ስብጥር ለማሳደግና የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋት የግል አልሚዎች እንዲሳተፉ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱን የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡ 

በየዓመቱ የሀገሪቱ የኃይል ፍላጎት በአስር በመቶ እያደገ  መሆኑን ያነሱት የተቋሙ የትራንስሚሽን እና ቢዝነስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አንዷለም ሲዓን፤ ከታሪፍ ማሻሽያው ጎን ለጎን የግል አልሚዎች እንዲሳተፉ ለማድረግ እየተሰራ  መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ይሁን እንጂ በሀገሪቱ ያለው ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ የታሪፍ ምጣኔ የግል አልሚዎችን የሚያበረታታ ባለመሆኑ እስከ አሁን የሚፈለገው ውጤት አለመገኘቱ ተገልጿል፡፡

ከአሁን ቀደም ተቋሙ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወስዶት የነበረውና በተቋሙ የፋይናንስ ቁመና ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮ የቆየውን ብድር መንግሥት ወደ ራሱ መውሰዱም ተነስቷል፡፡

ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ተቋሙ የመክፈል አቅሙንና ገቢውን ያገናዘበ ብድር ከባንኩ በመውሰድ ፕሮጀክቶችን በራሱ አቅም ለማስፈፀም እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
የኔታ ቲዮብ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...