ከ20 በላይ የጣሊያን ኩባንያዎች በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር በሚካሄደው ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡
ጣሊያን በኢትዮጵያ የምታደርገው ቀጥተኛ ኢንቨስትምንት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ ለአለም አቀፍ የንግድ እና የረጅም ጊዜ አጋርነት ምቹ እየሆነች መምጣቷን ያሳያል ሲል የጣሊያ የንግድ ኤጀንሲ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል፡፡
ለዚህም 723 ሚሊዮን ዩሮ የደረሰው የኢጣሊያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያደረጉት ኢንቨስትመነት ተጠቃሽ ነው ያለው ኤጀንሲው ይህም ለሰፋፊ የኢኮኖሚ ትብብር ማዕቀፍ አስተዋጽኦ እያበረከተ አንደሆነ ያሳያል ብሏል፡፡
በሁለቱ አገራት መካከል እያደገ የመጣው ይህ የኢኮኖሚ ትብብር ከሚያዝያ 15 አስከ ሚያዚያ 17/ 2028 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር በሚካሄደው ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ 2026 ላይ በጉልህ ይታያል ተብሏል፡፡
በዝግጅቱ ላይ ከ20 በላይ የጣሊያን ኩባንያዎች ከዓለም አቀፍ እና ከሀገር ውስጥ ተሳታፊዎች ኩባንያዎች ጋር ሆነው ይሳተፋሉ፡፡
ኢትዮጵያ በሯን ለአለም ንግድ ከፍት ማድረጓ እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እያደገ መምጣቱ በቀጠናው የኢኮኖሚ ማዕከልነት ያላትን ቦታ ይበልጥ እየጠነከረ መሆኑን ያሳያል ተብሏል።
በዚህም የተነሳ በርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በግንባታ፣ በመሠረተ ልማት፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በጨርቃጨርቅ፣ በግብርና ምርት ማቀነባበር እና አገልግሎቶች ባሉ ወሳኝ ዘርፎች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑ ተጠቅሷል።
እስካሁንም ወደ 150 የሚጠጉ የጣሊያን ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ ኩባንያዊች ጋር የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ፈጥረዋል ሲል ኤጀንሲው አስረድቷል፡፡
ኢትዮጵያ የጣሊያን “ማቴዪ ፕላን” በሚል የቀረጸችውና አገሪቱ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በዘላቂ ልማት ፕሮጀክቶች እና በኢኮኖሚ አጋርነት ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ስትራቴጂ አካል መሆኗን ሰምተናል፡፡
በዚህ ማዕቀፍ ስር ጣሊያን በኢትዮጵያ ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የኢኮኖሚ ዕድገት እና ዘላቂ የልማት ግቦቿን እንድታሳካ ለመደገፍ 25 ሚሊዮን ዮሮ ድጋፍ መድረጓን ከመግለጫው ላይ ተመልክተናል፡፡
ጣሊያን በኢትዮጵያ ውስጥ እየደረገች ያለው ኢንቨስትመንት በተለይ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ የስራ እድሎችን በግንባታ፣ በማኑፋክቸሪንግ እና ተዛማጅ ኢንዱስትሪዎች ፈጥረዋል ተብሏል፡፡
ከስራ አድል ፈጠራው በተጨማሪ የጣሊያን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መስራት ለሀገር ውስጥ አቅራቢዎች፣ ንዑስ ተቋራጮች፣ የሎጂስቲክስ አገልግሎት ሰጪዎችን እና የችርቻሮ አገልግሎቶች ሰጪዎች አን ለሌሎችም ከፍተኛ ድጋፍ አበርክቷል፡፡
የኢጣሊያ ኩባንያዎች በቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ላይ መሳተፋቸው የጣሊያን ኩባንያዎች በአፍሪካ ዋነኛ የግንባታ ማዕከል እያሆነች ወደ መጣቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በስፋቱ እንዲገቡ ፣ እንዲስፋፉ እና እንዲጠናከሩ ያስችላቸዋል ሲል አጣሊያን ንግድ ኤጀንሲ ጠቅሷል።
ኤግዚቢሽኑ ለንግድ ልማት፣ ለአጋርነት ግንባታ እና ከሀገር ውስጥ ገንቢዎች፣ ተቋራጮች እና ውሳኔ ሰጪዎች ጋር ጠንካራ መስተጋብር በመፍጠር ወደፊት ለሚመጡት የህዝብ እና የግል ፕሮጀክቶች ቀጥተኛ መዳረሻ ይሰጣል።
ኤግዚቢሽኑ ለንግድ ልማት፣ ለሽርክና ግንባታ እና ከሀገር ውስጥ አልሚዎች፣ ተቋራጮች እና ውሰኔ ሰጪዎች ጋር ጠንካራ ትስስር ለመፍጠር ዕድሎችን ይፈጥራል ተብሎ ታምኖበታል።
ሸገር 102.1
